መሃል ፡ ሰፋሪ (Mehal Sefari) - መዝሙረ ፡ ደረጀ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መዝሙረ ፡ ደረጀ
(Mezmure Dereje)

Mezmure Dereje 3.jpg


(3)

ጻድቅ ፡ ሆይ ፡ በርታ
(Tsadeq Hoy Berta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመዝሙረ ፡ ደረጀ ፡ አልበሞች
(Albums by Mezmure Dereje)

ስር ፡ ሳይሰድድብኝ ፡ ህመሜ ፡ ሳይጠና
ከሕይወት ፡ ወጥቶ ፡ መሞት ፡ አለና
እምቢ ፡ ያለውን ፡ ልቤን ፡ ግራው
እዚህም ፡ እዚያም ፡ ይገድላል ፡ በለው ፡ (፪)

መልኬ ፡ እየተቀየረብኝ
ዛሬ ፡ አንተን ፡ ነገ ፡ ዓለምን ፡ ሆነብኝ
ወይ ፡ አልበረድኩኝ ፡ ወይ ፡ አልሞቅኩኝ
እንዲያው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ ሆኛለሁኝ
መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ሆኛለሁኝ

መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ከአፍህ ፡ ይተፋል ፡ (፪)

አወይ ፡ ልቤ ፡ ተመለስ
ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ የሚወድህ ፡ (፪)

ከአፍህ ፡ መተፋት ፡ እጅግ ፡ ያስፈራል
ክፉ ፡ ልማዴን ፡ መጣል ፡ ይሻላል
እምቢ ፡ ያለውን ፡ ልቤን ፡ ግራው
እዚህም ፡ እዚያም ፡ ይገድላል ፡ በለው ፡ (፪)

መልኬ ፡ እየተቀየረብኝ
ዛሬ ፡ አንተን ፡ ነገ ፡ ዓለምን ፡ ሆነብኝ
ወይ ፡ አልበረድኩኝ ፡ ወይ ፡ አልሞቅኩኝ
እንዲያው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ ሆኛለሁኝ
መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ሆኛለሁኝ

መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ከአፍህ ፡ ይተፋል ፡ (፪)

አወይ ፡ ልቤ ፡ ተመለስ
ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ የሚወድህ ፡ (፪)

ልቤስ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ ሁለት ፡ ይመኛል ፡
እዚህም ፡ እዚያም ፡ ብሎ ፡ ያስቸግራል
እምቢ ፡ ያለውን ፡ ልቤን ፡ ግራው
እዚህም ፡ እዚያም/የግብጽ:ሽንኩርት ፡ ይገድላል ፡ በለው ፡ (፪)

መልኬ ፡ እየተቀየረብኝ
ዛሬ ፡ አንተን ፡ ነገ ፡ ዓለምን ፡ ሆነብኝ
ወይ ፡ አልበረድኩኝ ፡ ወይ ፡ አልሞቅኩኝ
እንዲያው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ ሆኛለሁኝ
መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ሆኛለሁኝ

መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ከአፍህ ፡ ይተፋል ፡ (፪)

አወይ ፡ ልቤ ፡ ተመለስ
ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ የሚወድህ ፡ (፪)