ይፍሰስ (Yifses) - መዝሙረ ፡ ዳዊት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መዝሙረ ፡ ዳዊት
(Mezmure Dawit)

Lyrics.jpg


(Volume)

ይፍሰስ
(Yifses)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2020)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 04:59
ጸሐፊ (Writer): መዝሙረ ፡ ዳዊት
(Mezmure Dawit
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመዝሙረ ፡ ዳዊት ፡ አልበሞች
(Albums by Mezmure Dawit)

[መግቢያ]
ይፍሰስ ከዋናው ከሰማይ ከላይ ከአንተ ዘንድ
ቀላያት ይነደሉ ከምንጩ መንፈስህ ይውረድ
ያረስርስ ደረቁን ምድር የተጠማ በመንፈስህ ያብብ
ኃይል አለው ስምህ መንፈስህ ሥልጣን አለው መንፈስህ

ወደ እውነት ይመራ ዘንድ የሕይወትን መንገድ
ወደ እውነት ይመራ ዘንድ ወደ ሕይወት መንገድ
ወደ እውነት ይመራ ዘንድ የሕይወትን መንገድ
ወደ እውነት ይመራ ዘንድ ወደ ሕይወት መንገድ

[ቁጥር 1]
ከላይ የወረደው ከአንተ የተላከው
ፈስሶ እንደዚሁ ማንስ ሊያስመልሰው
ላይተክል ላይሰራ ላያፈራ ላያለመልም
አውቃለሁ መንፈስህ እንዲሁ አይመጣም

[አዝ]
ላይተክል ላይሰራ ላያፈራ ላያለመልም
አውቃለሁ መንፈስህ እንዲሁ አይመጣም

በመሰዊያዉ ላይ ይንደድ እሳቱ
ክብርህ ይምጣ ይፍጠን ሰዓቱ
በመሰዊያው ላይ ይንደድ እሳቱ
ክብርህ ይምጣ ይፍጠን ሰዓቱ

[ቁጥር 2]
የተጨነቀች ነፍስ መንፈስህ ሲመጣ
ይታይ ሁኔታዋ ስቃይዋንም ትርሳ
በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ የምድሩ የለም
ሚሸተዉ ሕይወት ነው ቀን ሌትም ዘላለም

[አዝ]
ላይተክል ላይሰራ ላያፈራ ላያለመልም
አውቃለሁ መንፈስህ እንዲሁ አይመጣም

ያረስረስ ደረቁን ምድር የተጠማ በመንፈስህ ያብብ
ኃይል አለው ስምህ መንፈስህ

ወደ እውነት ይመራ ዘንድ የሕይወትን መንገድ
ወደ እውነት ይመራ ዘንድ ወደ ሕይወት መንገድ
ወደ እውነት ይመራ ዘንድ የሕይወትን መንገድ
ወደ እውነት ይመራ ዘንድ ወደ ሕይወት መንገድ

በመሰዊያው ላይ ይንደድ እሳቱ
ክብርህ ይምጣ ይፍጠን ሰዓቱ
በመሰዊያዉ ላይ ይንደድ እሳቱ
ክብርህ ይምጣ ይፍጠን ሰዓቱ