From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem Getu)
|
|
፫ (3)
|
Ya Messih (Ya Messih)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፰ (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፩ (11)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:43
|
ጸሐፊ (Writer):
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem GetuProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች (Albums by Meskerem Getu)
|
|
አያጓጓኝም ሌላው ሌላው ነገር
ሌላው ሌላው ነገር
ይቅር የቀረው ካንተ በቀር/3
በጌተሰማኒ ለከፋው ስቃይህ
ለአባትህ ፈቃድ ታዘህ እንደጨረስህ
እግሬ ይሩጥልህ ይገዛ ጉልበቴ
በውድ ዋጋ ላንተ ተሽጧል ህይወቴ
ኦሆ ይገባሃል ስለኔ ሞተሃል
ኦሆ ይገባሃል ስለኔ ታመሃል
ኦሆ ይገባሃል ስለኔ ስቃዬን ወስደሃል
ኦሆ ይገባሃል ስለኔ ህመሜን ታመሃል
የጓጓሁለት ከፈቃድህ ካወጣኝ ከለየኝ
ጤና አይሆነኝም አያረካኝ ባዶነቴን አይሞላኝ
የተመኘሁት ይቅርብኝ ይቅርብኝ ይቅርብኝ
እየሱስዬ ቅርልኝ ቅርልኝ ቅርልኝ
የጓጓሁለት ያምልጠኝ ያምልጠኝ ያምልጠኝ
እየሱስ አንተ ትረፈኝ ትረፈኝ ትረፈኝ
እየሱስ መድሃኒቴ እየሱስ ህይወቴ
እየሱስ ዘላለሜ እየሱስ እምነቴ
እየሱስ መንገዴ እየሱስ ዘላለሜ
እየሱስ ህይወቴ እየሱስ እምነቴ
ከጊዜያዊ ደስታ መነፈቅን መርጦ
ከግብፅ ገንዘብ ይልቅ አንተን አስበልጦ
ሙሴ በፈርዖን ስም እንዳይጠራ
በእምነት እምቢ አለ ፀና ካንተ ጋራ
ኦሆ ትበልጣለህ አንተኮ ትልቅ ነህ
ኦሆ ትልቃለህ በምን ትተካለህ
ኦሆ ትበልጣለህ አንተኮ ህይወት ነህ
ኦሆ ትልቃለህ አንተ ዘላለም ነህ
|