ያህዌ (Yahweh) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 3.jpg


(3)

Ya Messih
(Ya Messih)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2024)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:33
ጸሐፊ (Writer): መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ቅዱስ/4 ሃያል/4
ኤሎሂም ኤሎሂም ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ
አልፋ ኦሜጋ አዶናይ አዶናይ

በመቅደስህ ተወደስ በሃይል ጠፈር ተወደስ
በችሎትህ ተወደስ የኛ እግዚአብሔር ተወደስ

ከፀሃይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ
በስልጣን ላለኸው አምልኳችን ይድረስ
ከፀሃይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ
በክብር ላለኸው አምልኳችን ይድረስ

ያሕዌ/3 የእስራኤል አምላክ ዛሬም አንተ አንተ ነህ
ኤሎሂም/3 የአብርሃም አምላክ ዛሬም አልደከምክም

ልዩ ልዩ አምላክ የተለየህ/2

በቅድስና ሚመስልህ የለም
የተለየህ ነህ የተለየህ
ሚቀራረብህ ሚያክልህ የለም
የተለየህ ነህ የተለየህ
አትመሰልም ምሳሌ የለህ
የተለየህ ነህ የተለየህ
አንተ ራስህን አንተን መሳይ ነህ
የተለየህ ነህ የተለየህ

ቅዱስ/4 ሃያል/4
ኤሎሂም ኤሎሂም ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ
አልፋ ኦሜጋ አዶናይ አዶናይ

በመቅደስህ ተወደስ በሃይል ጠፈር ተወደስ
በችሎትህ ተወደስ የኛ እግዚአብሔር ተወደስ