ተናገር (Tenager) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Lyrics.jpg


(3)

Ya Messih
(Ya Messih)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2024)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:52
ጸሐፊ (Writer): መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ፈልጌህ መጥቻለው ፈልጌህ ፈልጌህ
ልገኝህ መጥቻለው እየሱስ ላገኝህ
ናፍቀኸኝ መጥቻለው ልሰማህ ልሰማህ
ፈልጌህ መጥቻለው እየሱስ ላደምጥህ

አንተ ለብቻህን እንድትደመጥ
የስጋዬ ጩኸቱ እረጭ ይበል ፀጥ
አንተ ለብቻህን እንድትደመጥ
የምኞቴ ጩኸቱ እረጭ ይበል ፀጥ

ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው አለው በለኝ
ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው ይኸው በለኝ

የልብህን ሃሳብ እስኪ አጫውተኛ
ሁንልኝ የህይወቴ መካከለኛ
ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች
በኔም ላይ እንድትሆን ላሳብህ ለመች ለአንተ ልምች

ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው አለው በለኝ
ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው ይኸው በለኝ

ብቸኛ አቅሜ የምታደርገኝ ቀና
በአንተ ካልሆነ ከቶ አልድንምና
ምትለኝን ሁሉ ላደምጥህ ፈልጌ
በፊትህ ስር እሆናለሁ ራሴን ባዶ አድርጌ
ራሴን ባዶ አድርጌ

ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው አለው በለኝ
ተናገር ተናገረኝ አባ ድምፅህን አሰማኝ
በእጆችህም ዳሰኝ ልጄ አለው ይኸው በለኝ