ምንም አይሳንህም (Minim Ayisanihim) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Lyrics.jpg


(3)

Ya Messih
(Ya Messih)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2024)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:40
ጸሐፊ (Writer): መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

አንተን ተስፋ አድርጌ ፀልዬ ነበረ
ፀሎቴን ሰምተሃል ስለቴ ሰመረ
አንተን ተስፋ ተማምኜ ተስዬ ነበረ
ጩኸቴን ሰምተሃል ስለቴ ሰመረ

ፀሎትን ትሰማለህ እንባንም ታብሳለህ
ለሚጠሩህ ቅርብ ነህ ደጅህን ትከፍታለህ

ኡ አንዳንድ ጊዜ እታወካለሁ
የሚነፍሰው ነፋስ ታንኳዬን ሲንጠው
ኡ መርከቤ ላይ ጌታዬ ተኝተህ
ይሄ ሁሉ ሲሆን አታይም ወይ ነቅተህ

ሚሆነው ሳይገባኝ ተጨንቄ ሳምጥ
ታንኳዬ በውሃ ሲሞላ ስናወጥ
ማዕበል ሚታዘዝ ህ ሚሰማህ ወጀቡ
በተነሳህ ጊዜ ግን ያወኩኝ ዝም አሉ

ምንም ምንም አይሳንህም
የማመልክህ አምላክ ትችላለህ ሁሉንም
ምንም ምንም አያቅትህም
የታመንኩህ ጌታ ትችላለህ ሁሉንም

ኡ ባለመዳኒት ያልተገኘላት
ላአስራ ሁለት አመት ደም እየፈሰሳት
ኡ ተንከራታች ንብረቷንም ሰታ
ማንም አልተገኘም ችግሯን ሚፈታ

ከህዝብ ሁሉ መሃል በእምነት ተጋፍታ
ፈውሷን ተቀበለች የልብስህን ጫፍ ነክታ
ለስንቱ መለኛ ላዋቂ ያቃተ
ድንቅ መካር ሃያል ቀላል ነው ለአንተ

ምንም ምንም አይሳንህም
የማመልክህ አምላክ ትችላለህ ሁሉንም
ምንም ምንም አያቅትህም
የታመንኩህ ጌታ ትችላለህ ሁሉንም