From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem Getu)
|
|
፫ (3)
|
Ya Messih (Ya Messih)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፰ (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፩ (1)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:15
|
ጸሐፊ (Writer):
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem GetuProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች (Albums by Meskerem Getu)
|
|
የልቤ አምላክ ሁሉ ነገሬ
እየመራኸኝ ባንተ ተምሬ
ከራሴ መንገድ እየመለስከኝ
የማይታለፈውን አሻገርከኝ
ጌታ ምህረትህ እጅግ ብዙ ብዙ ነው ጌታ ምህረትህ
አቤት ይቅርታህ እጅግ ብዙ ብዙ ነው አቤት ይቅርታህ
አቤት ደግነትህ መጨረሻ የለው ለደግነትህ
እርህራሔህ መጨረሻ የለው እርህራሔህ
ላመስግንህ እስኪ ላመስግንህ
ለውለታህ ምላሽ እንኳን ባይመጥንህ
ላመስግንህ ውዴ ላመስግንህ
ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ
ከተጠመደብኝ ወጥመድ አስመልጠህ
ከክፉ ውሳቤ ልቤን እኔን ጠብቀህ
ቃልህን እየላክ አባ እየመከርከኝ
ከጠላቴ አጥፊ እቅድ ፈጥነህ አዳንከኝ
ተመስገን አባ ተመስገን
ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ
ተባረክ ውዴ ተባረክ
ለውለታህ ምላሽ ምስጋናን ላብዛልህ
በጭንቅ ቀኖቼ ሁሉ ከጎኔ ነህ
ስብራቴን ሳካፍልህ መቼ ደከመህ
ሁሉ በተወኝም ጊዜ የትም አልሄድህ
በጊዜ ብዛት አይላላም ወዳጅነትህ
ተመስገን አባ ተመስገን
ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ
ተባረክ አባ ተባረክ
ለውለታህ ምላሽ ምስጋናን ላብዛልህ
በምድረበዳ ሸለቆ አሰልጥነህ
የጨከንክብኝ ሲመስለኝ ቀርበህ አባብለህ
ሁሉ ለበጎ ሲቀየር በአይኔ እያየሁ
ለመልካም ስላስጨነከኝ አከብርሃለው
ተመስገን አባ ተመስገን
ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ
ተባረክ አባ ተባረክ
ለውለታህ ምላሽ ምስጋናን ላብዛልህ
|