From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem Getu)
|
|
፫ (3)
|
Ya Messih (Ya Messih)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፰ (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፭ (5)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:05
|
ጸሐፊ (Writer):
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem GetuProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች (Albums by Meskerem Getu)
|
|
አቤት ውበቱ ክርስትና
የምንጠብቀው አለንና
አቤት ሲያምር ክርስትና
ጉዞ ወደ ፅዮን ነውና
አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ
መንገድህ ድንቅ ነው ጌታ ስትመራ
አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ
መንገድህ ልዩ ነው ጌታ ስትመራ
የፅድቅ ጉዞ እንዴት ያምራል
ምክር ግሳፄህ እንዴት ያምራል
ማፅናናት ፍቅርህ እንዴት ያምራል
ቅጣት ቁንጥጫህ እንዴት ያምራል
መስቀልህን ይዞ አንተን መከተሉ
ቢያምም ይጣፍጣል መታገስ በሁሉ
ለድል ሰንደቅ ጉዞ ብናልፍ በመከራ
ምሽቱ ሊያበቃ ጥቂት ቀርቷልና
አቤት ሲያምር ክርስትና
ጉዞ ወደ ክብር ነውና
አቤት ወበቱ ክርስትና
የምንጠብቀው አለንና
አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ
መንገድህ ድንቅ ነው ጌታ ስትመራ
አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ
መንገድህ ልዩ ነው ጌታ ስትመራ
ታግሶ የሄደ ባንተ የተመራ
በፀጋህ ታግዞ ጦርነት ሳይፈራ
ሰልፍ ሳያስቆመው እየገሰገሰ
የይሁዳ አንበሳ አንተን አነገሰ
አቤት ውበቱ ክርስትና
የምንጠብቀው አለንና
አቤት ሲያምር ክርስትና
ጉዞ ወደ ፅዮን ነውና
አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ
መንገድህ ድንቅ ነው ጌታ ስትመራ
አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ
መንገድህ ልዩ ነው ጌታ ስትመራ
|