From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem Getu)
|
|
፫ (3)
|
Ya Messih (Ya Messih)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፰ (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፱ (9)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:30
|
ጸሐፊ (Writer):
|
መስከረም ፡ ጌቱ (Meskerem GetuProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች (Albums by Meskerem Getu)
|
|
በክብች ወዳረግከው አሳባችን እየሄደ
ምዝገባችን ወዳለበት ልባችን እየነጎደ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ እየሱስ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን አትመጣም ወይ እየሱስ
የመለከት ድምፅ እስክንሰማ
ስትወርድ ልናይህ በክብር በደመና
በጥልቅ ናፍቆት ወደላይ እናያለን
መሲሃችን ሆይ እባክህ ቶሎ ናልን
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ እየሱስ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን አትመጣም ወይ እየሱስ
አሜም ቶሎ ና የኛ ጌታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ማራናታ ቶሎ ና
አሜም ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
ከሙታን መንደር ልጆችህን የጠራህ
የንጋት ኮከብ ለጠፋነው የበራህ
በመደላደል ረስተንህ አንቀመጥ
መዳኒታችን ዳግመኛ እስክትገለጥ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ እየሱስ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን አትመጣም ወይ እየሱስ
አሜም ቶሎ ና የኛ ጌታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ማራናታ ቶሎ ና
አሜም ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
|