አሸናፊ ነው (Ashenafi New) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 3.jpg


(3)

Ya Messih
(Ya Messih)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2024)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 3:36
ጸሐፊ (Writer): መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

እግዚአብሔር ተዋጊ ስሙ እግዚአብሔር ነው
በዘመናት መሃል ተፈርቶ የኖረው
የተሰወረውን ሚስጥር የሚገልጥ
በሃይልና ብርታት ከሁሉ የሚበልጥ

አሸናፊ ነው የኛ ጌታ
አሸናፊ ነው ሁሉን ሚረታ
አሸናፊ ነው ክንደብርቱ
ማብቂያ የሌለው ለመንግስቱ

ባለግርማ የተፈራ ቀኙ በሃይል የከበረ
ሁልግዜ እየረታ እያሸነፈ የኖረ
የተነሱበትን ቀጪ ቁጣውን እየሰደደ
በሰማይ በምድር የለም ደፍሮት በደህና የሄደ

አሸናፊ ነው የኛ ጌታ
አሸናፊ ነው ሁሉን ሚረታ
አሸናፊ ነው ክንደብርቱ
ማብቂያ የሌለው ለመንግስቱ

ከግብፃዊያን ምድር ህዝቦቹን ያወጣ
ያስገበራቸውን ፈርዖንን የቀጣ
የሰራዊት አምላክ ገናና ስመኛ
ክንዱን የሚሞክር የለው ወደረኛ
የሰራዊት አምላክ ገናና ስመኛ
ክንዱን የሚሞክር የለው ወደረኛ

የማይመረመረውን ድንቅ ታላቅ ነገር ሰሪ
ሁሉ የሚታዘዙለት የሌለው ተከራካሪ
ወደሱ ሮጠው ለመጡ የሚያስጠልል ነው መሸሻ
ቅጥርን አዘላይ መከታ ለታመኑት የሚሆን ጋሻ

አሸናፊ ነው የኛ ጌታ
አሸናፊ ነው ሁሉን ሚረታ
አሸናፊ ነው ክንደብርቱ
ማብቂያ የሌለው ለመንግስቱ