አንድ ንጉስ (Aned Nigus) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 3.jpg


(3)

Ya Messih
(Ya Messih)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2024)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:16
ጸሐፊ (Writer): መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

አንድ ንጉስ አንድ ብቻ
በሰማይ በምርድ የሌለው አቻ
አንድ ንጉስ አርሱ ብቻ
በሰማይ በምርድ የሌለው አቻ

በራሱ ላይ ዘውድ የጫነው
የነገስታት ሁሉ ንጉስ ነው
በአምባው ላይ የተቀመጠው
የጌቶቹ ሁሉ ጌታ ነው

እናመልከዋለን አሜን የሆነውን እንሰግድለታለን
እናከብረዋለን ጌታ እየሱስን እንሰግድለታለን

ሃያል አምላክ የዘላለም አባት ተብሎ የተጠራ
አለቅነት በጫንቃው ላይ ያለ ግርማዊ የሚያስፈራ
ከእግሩ በታች ሁሉ ሚገዛለት የቤተክርስቲያን ራስ
መንግስቱ ከላይ ጠቅልሎ የሚገዛ ጌታችን እየሱስ

በራሱ ላይ ዘውድ የጫነው
የነገስታት ሁሉ ንጉስ ነው
በአምባው ላይ የተቀመጠው
የጌቶቹ ሁሉ ጌታ ነው

እናመልከዋለን አሜን የሆነውን እንሰግድለታለን
እናከብረዋለን ጌታ እየሱስን እንሰግድለታለን

የእግዚአብሔር በግ የእስራኤል ንጉስ እውነተኛ አምላክ
ገና ከጥንት እሱ እሱ የሆነ የኖረ ሲመለክ
መላዕክቱ ከእግሩ ስር ወድቀው ቅዱስ ቅዱስ ሚሉት
በምድር የሚኖሩ በእጁ ያበጃቸው ሁሉ ሚሰግዱለት

አንድ ንጉስ አንድ ብቻ
በሰማይ በምርድ የሌለው አቻ
አንድ ንጉስ አርሱ ብቻ
በሰማይ በምርድ የሌለው አቻ

በራሱ ላይ ዘውድ የጫነው
የነገስታት ሁሉ ንጉስ ነው
በአምባው ላይ የተቀመጠው
የጌቶቹ ሁሉ ጌታ ነው

እናመልከዋለን አሜን የሆነውን እንሰግድለታለን
እናከብረዋለን ጌታ እየሱስን እንሰግድለታለን