የጌታ ፡ ውድ ፡ ልጅ (Yegieta Wud Lej) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

የመዳን ፡ ሚስጢር ፡ ትፈቶልህ
ኢየሱስ ፡ ነግቶ ፡ በትላንትህ
በፍቅሩ ፡ ስንቴ ፡ ተጽናንተሃል
ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ከጐንህ ፡ ቆሞልሃል
ዛሬ ፡ ምን ፡ ስንፍና ፡ ተበተበህ
አጥርተህ ፡ እንዳታይ ፡ ዓይንህን ፡ ከለለህ
ከዘላለሙ ፡ ይልቅ ፡ ለሚያልፈው ፡ ተገኘህ
ጌታን ፡ በመተውህ ፡ እንደምን ፡ ተሞኘህ

 አዝ፦ የጌታ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ
         ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ
        የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ
       ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ

ብርሃንን ፡ ትተህ ፡ ወደ ፡ ጨለመበት ፡ ትገሰግሳለህ
የነፍስህን ፡ ሰላም ፡ ከማታገኝበት ፡ ሰፈር ፡ ትሮጣለህ
ምንስ ፡ ብትኮበልል ፡ ከኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ወዴት ፡ ትሸሻለህ
ለአንተ ፡ ሲል ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠልህ ፡ በመስቀል ፡ የወለ

አዝ፦ የአባቴ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ
         ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ
        የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ
        ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ

የመዳን ፡ ሚስጢር ፡ ትፈቶልህ
ኢየሱስ ፡ ነግቶ ፡ በትላንትህ
በፍቅሩ ፡ ስንቴ ፡ ተጽናንተሃል
ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ከጐንህ ፡ ቆሞልሃል
ዛሬ ፡ ምን ፡ ስንፍና ፡ ተበተበህ
አጥርተህ ፡ እንዳታይ ፡ ዓይንህን ፡ ከለለህ
ከዘላለሙ ፡ ይልቅ ፡ ለሚያልፈው ፡ ተገኘህ
ጌታን ፡ በመተውህ ፡ እንደምን ፡ ተሞኘህ

 አዝ፦ የጌታ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ
         ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ
        የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ
       ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ

እንዴት ፡ ሊሆን ፡ ሰበብ ፡ የአንተ ፡ መገፋት ፡ ቢነሳብህ ፡ ዱላ
ይከፍል ፡ የለ ፡ ወይ ፡ ለሁሉ ፡ እንደስራው ፡ ብትታገስ ፡ ኋላ
ወንድሜ ፡ ተመለስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ሚበጅህ ፡ ምን ፡ ቢበዛ ፡ ሰልፉ
ዛሬም ፡ ይወድሃል ፡ ፍቅሩ ፡ አልቀነሰም ፡ ግባ ፡ ወደ ፡ እቅፉ

 
አዝ፦ የአባቴ ፡ ውድ ፡ ልጅ ፡ የገዛህ ፡ በደሙ
         ካሰረህ ፡ እስራት ፡ ያድንሃል ፡ ስሙ
        የተበትበህን ፡ በጣጥሰህ ፡ ተራመድ
        ከነፍስህ ፡ አብልጠህ ፡ ዓለም ፡ አትውደድ