From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ተሰሚ ፡ ነህ ፡ በሰማይ ፡ በምድር
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ሚንበረከክልህ
የፈጠርከን ፡ እንሰግድልሃለን
ሞገስህን ፡ ክብርህን ፡ እያየን
ይሹሩን ፡ ሆይ ፡ በሰማያት ፡ ላይ ፡ ለእረድኤትህ
በደመናት ፡ ላይ ፡ እንደሚሄድ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
ኧረ እንደርሱ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም (፪x)
ዘመንህ ፡ ዘላለም ፡ ከቶ ፡ አታረጅም
አምሳያ ፡ የለህም ፡ መቼም ፡ አትተካም
አዬዬ ፡ መቼም ፡ አትተካም
ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ በሀይል ፡ የሚያበራ
ከዋክብት ፡ ጨረቃን ፡ ደመናን ፡ የሰራህ
አዬዬ ፡ ፀሐይን፡ የሰራህ
የአማልክቱ ፡ አምላካቸው ፡ ነህ
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ የዓለማት ፡ ንጉሥ ፡ ነህ
ወሰን ፡ የሌለህ ፡ ስራህ ፡ እረቂቅ
የማትታወቅ ፡ የሆንህ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም
ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም
ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም
ተሰሚ ፡ ነህ ፡ በሰማይ ፡ በምድር
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ሚንበረከክልህ
የፈጠርከን ፡ እንሰግድልሃለን
ሞገስህን ፡ ክብርህን ፡ እያየን
ይሹሩን ፡ ሆይ ፡ በሰማያት ፡ ላይ ፡ ለእረድኤትህ
በደመናት ፡ ላይ ፡ እንደሚሄድ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም (፪x)
የዓለም ፡ ሁሉ ፡ መሪ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ሀይለኛ
ከሁሉ ፡ ቀዳሚ ፡ የሌለህ ፡ ፊተኛ
አዬዬ ፡ የሌለህ ፡ ፊተኛ
ይሁን ፡ ባልከው ፡ ቃልህ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጠረ
እቅድህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ስራህም ፡ ያማረ
አዬዬ ፡ ስራህም ፡ ያማረ
የአማልክቱ ፡ አምላካቸው ፡ ነህ
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ የዓለማት ፡ ንጉሥ ፡ ነህ
ወሰን ፡ የሌለህ ፡ ስራህ ፡ እረቂቅ
የማትታወቅ ፡ የሆንህ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም
ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም
ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x)
|