መለሰን (Melesen) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

እንጀራ ፡ ልንበላ ፡ አልተከተልንህም
ሃብት ፡ ብልጥግና ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አልጠራንም
ለምድር ፡ በረከት ፡ ታይቶ ፡ ለሚጠፋ
መች ፡ ደምህ ፡ ፈሰሰ ፡ ለሚያልፍ ፡ ተስፋ
የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ ማግኘታችን ፡ ጉዳይ
ሁሌም ፡ ብርቃችን ፡ ነው ፡ ከምን ፡ ጋር ፡ ሊተያይ
ሕይወት ፡ ያካፈልከን ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
ሌላ ፡ አላየንም ፡ በነፍሱ ፡ የጨከነ

ግን ፡ ዛሬ ፡ ሲመጣ ፡ በየአደባባዩ
ትኩረት ፡ የሚፈልግ ፡ የሚል ፡ እኔን ፡ እዩ
አንተን ፡ አደብዝዞ ፡ ራሱን ፡ የሚያጐላ
አባብሎ ፡ ወሰደን ፡ ሆነናል ፡ ተላላ

  አዝ፦ አቤቱ ፡ ሕዝብህን ፡ መልሰን
           ሳንጠፋ ፡ ቀድመህ ፡ ድረስልን
           አቤቱ ፡ ልጆችህን ፡ አስበን
           ከድፍረት ፡ ከውድቀት ፡ ታደገን

በጐ ፡ በሚመስል ፡ ሃሳብ ፡ እየተሳበ
በመልካም ፡ ንግግር ፡ ሕዝብ ፡ ተሰበሰበ
ዓመጸ ፡ ማይከለክል ፡ የረሳ ፡ ፍርድህን
እራሳችንን ፡ እንዳናይ ፡ አደንዝዞ ፡ አሰረን
በዘመን ፡ ፍጻሜ ፡ ጫፍ ፡ ላይ ፡ ሆነን ፡ ሳለን
ልባችን ፡ እንዳያይ ፡ ምንው ፡ ተደለለ
ዘይታችንን ፡ እንሙላ ፡ ጊዜው ፡ ሳይገባደድ
ፈጥነን ፡ እንመለስ ፡ ከሄድንበት ፡ መንገድ

   አዝ፦ አቤቱ ፡ ሕዝብህን ፡ መልሰን
           ሳንጠፋ ፡ ቀድመህ ፡ ድረስልን
           አቤቱ ፡ ልጆችህን ፡ አስበን
           ከድፍረት ፡ ከውድቀት ፡ ታደገን