ለኔ ያለህ ፡ ትኩረት (Lenie Yaleh Tekuret) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ለኔ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ያስገርመኛል
ለኔ ፡ ያለህ ፡ ምህረት ፡ ያስደንቀኛል
ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትዕግሥት ፡ ያስገርመኛል
ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትኩረት ፡ ያስደንቀኛል

     መተላለፌን ፡ ደምስሰህ ፡ ተቀበልከኝ
     በመንገዴ ፡ እንድጠፋ ፡ መቼ ፡ ተውከኝ
     ከፊቴ ፡ ሆነህ ፡ እግሮቼን ፡ የምትመራ
     ስጋቴን ፡ ሰብረህልኛል ፡ እንዳልፈራ

በጎ ፡ ስጦታ ፡ ፍፁም ፡ በረከት
ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሆኖልኛል ፡ በምህረት
በነፍስህ ፡ የገዛሃት ፡ ይቺ ፡ ነፍሴ
ምሥጋናህን ፡ አትረሳም ፡ ሁልጊዜ

አዝ፦ ለኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ያስገርመኛል
ለኔ ፡ ያለህ ፡ ምህረት ፡ ያስደንቀኛል
ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትዕግሥት ፡ ያስገርመኛል
ለኔ ፡ ያለህ ፡ ትኩረት ፡ ያስደንቀኛል

የውስጤን ፡ ነገር ፡ ምነግርህ ፡ የማወጋህ
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ተማምኖ ፡ ተረጋጋ
አሳረፍከኝ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ተመልክተህ
ጩኸቴን ፡ የሚሰማ ፡ ማን ፡ እንዳንተ

በጎ ፡ ስጦታ ፡ ፍፁም ፡ በረከት
ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሆኖልኛል ፡ በምህረት
በነፍስህ ፡ የገዛሃት ፡ ይቺ ፡ ነፍሴ
ምሥጋናህን ፡ አትረሳም ፡ ሁልጊዜ