From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሰው ፡ ሰው ፡ የሆነበት ፡ የሚኖርበት ፡ ምክንያት ፡ ካልገባው
በአካል ፡ ኖረ ፡ እንጂ ፡ የነፍሱን ፡ ክፍተት ፡ በምን ፡ ሊሞላው
ኑሮን ፡ ለማሸነፍ ፡ እሮጦ ፡ እሮጦ ፡ ቢደርስ ፡ ከግቡ
ተሳካለት ፡ ቢባል ፡ ሃሳቡ ፡ ሞልቶ ፡ እንዲያው ፡ ለደንቡ
ግን ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ የሕይወት ፡ ትርጉሙ
ከማግኘት ፡ ይበልጣል ፡ ለተፈለጉበት ፡ መገኘት ፡ በውሉ
ሃብትን ፡ ለማካበት ፡ ከመባዘን ፡ ይልቅ
ለምን ፡ እንደምንኖር ፡ በተጋን ፡ ለማወቅ
አዝ፦ ለምንድነው ፡ የምንኖረው
እስትንፋሳችን ፡ የሚቀጥለው
ዘመን ፡ ሲጨመር ፡ በእድሜያችን ፡ ላይ
ለሰራን ፡ ጌታ ፡ እንድንሰራ ፡ አይደል ፡ ወይ (፪x)
እርካታ ፡ በገንዘብ ፡ በመብል ፡ መጠጥ ፡ ከተገደበ
በጉብዝናው ፡ ጊዜ ፡ የፈጠረውን ፡ ሰው ፡ ካላሰበ
ኋላ ፡ በእድሜው ፡ ምሽት ፡ እንዳይጸጸት ፡ ከአሁኑ ፡ ይንቃ
የተፈለገበትን ፡ ምክንያት ፡ ያግኝ ፡ ቀኑ ፡ ሳያበቃ
በምድር ፡ ላይ ፡ ያስገኘን ፡ በሰማያት ፡ ያለ
አላማ ፡ ሰጥቶናል ፡ የምንኖርብት ፡ ከቁስ ፡ በዘለለ
ሁሉም ፡ በየድርሻው ፡ በተሰጠው ፡ ስራ
ለመፈጸም ፡ ይሩጥ ፡ የአምላክን ፡ አደራ
አዝ፦ ለምንድነው ፡ የምንኖረው
እስትንፋሳችን ፡ የሚቀጥለው
ዘመን ፡ ሲጨመር ፡ በእድሜያችን ፡ ላይ
ለሰራን ፡ ጌታ ፡ እንድንሰራ ፡ አይደል ፡ ወይ (፪x)
ሰው ፡ ሰው ፡ የሆነበት ፡ የሚኖርበት ፡ ምክንያት ፡ ካልገባው
በአካል ፡ ኖረ ፡ እንጂ ፡ የነፍሱን ፡ ክፍተት ፡ በምን ፡ ሊሞላው
ኑሮን ፡ ለማሸነፍ ፡ እሮጦ ፡ እሮጦ ፡ ቢደርስ ፡ ከግቡ
ተሳካለት ፡ ቢባል ፡ ሃሳቡ ፡ ሞልቶ ፡ እንዲያው ፡ ለደንቡ
ግን ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ የሕይወት ፡ ትርጉሙ
ከማግኘት ፡ ይበልጣል ፡ ለተፈለጉበት ፡ መገኘት ፡ በውሉ
ሃብትን ፡ ለማካበት ፡ ከመባዘን ፡ ይልቅ
ለምን ፡ እንደምንኖር ፡ በተጋን ፡ ለማወቅ
አዝ፦ ለምንድነው ፡ የምንኖረው
እስትንፋሳችን ፡ የሚቀጥለው
ዘመን ፡ ሲጨመር ፡ በእድሜያችን ፡ ላይ
ለሰራን ፡ ጌታ ፡ እንድንሰራ ፡ አይደል ፡ ወይ (፫x)
|