ፍቅር ፡ ነህ (Feqer Neh) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

የዘላለም ፡ አምላክ ፡ የትውልድ ፡ መጠጊያ
የፍጥረት ፡ መጋቢ ፡ ድጋፍ ፡ መሸሸጊያ
ልጅህን ፡ በመስጠት ፡ ፍቅርን ፡ የተገበርክ
ዓለሙን ፡ በሙሉ ፡ እንዲሁ ፡ የወደድክ

ፍቅር ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር
ይቅር ፡ ባይ ፡ የምትምር
እልፍ ፡ ነው ፡ ቸርነትህ
አይቆጠር (አይነገር )፡ ማጽናናትህ
(፪x)

ፍቅር ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ እያልኩ ፡ ባዜምልህ
ደግሞ ፡ በአዲስ ፡ ምሕረት ፡ ታስደንቀኛለህ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እልሃለው ፡ እጠራሃለው ፡ ደግሜ
ልዩ ፡ ነው ፡ አወዳደድህ ፡ ላዚምልህ ፡ ፊትህ ፡ ቆሜ

ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነህ
እንዴት ፡ ያለህ ፡ መሃሪ(ወዳጅ) ፡ ነህ
(፪x)

የዘላለም ፡ አምላክ ፡ የትውልድ ፡ መጠጊያ
የፍጥረት ፡ መጋቢ ፡ ድጋፍ ፡ መሸሸጊያ
ልጅህን ፡ በመስጠት ፡ ፍቅርን ፡ የተገበርክ
ዓለሙን ፡ በሙሉ ፡ እንዲሁ ፡ የወደድክ

ፍቅር ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር
ይቅር ፡ ባይ ፡ የምትምር
እልፍ ፡ ነው ፡ ቸርነትህ
አይቆጠር (አይነገር )፡ ማጽናናትህ
(፪x)

የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ ፡ ፍቅርን ፡ ለተጠማ
የምታለመልም ፡ ነፍስን ፡ የምታረካ
አውርቼ ፡ አውርቼ ፡ አልጠግብም ፡ አይገልጽህም ፡ ቃላቴ
ደግነትህን ፡ ብዘምር ፡ አልገልጸውም ፡ በዚህ ፡ አንደበቴ

ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነህ
እንዴት ፡ ያለህ ፡ መሃሪ(ወዳጅ) ፡ ነህ
(፪x)