From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ወደፊት ፡ እንደርሳለን ፡ በአዳዲስ ፡ ምሥጋና
ከልባችን ፡ በደስታ ፡ ልንሰግድልህ ፡ እንደገና
እያመለክን ፡ ልናመልክህ ፡ እናብዛልህ ፡ ብዙ ፡ ቅኔ
ከሃጥያት ፡ ስለፈታኸን ፡ ስለወጣን ፡ ከኩነኔ (፪x)
እንደገና (፯x)
በአዲስ ፡ ምሥጋና
እንደገና (፯x)
በአዲስ ፡ ምሥጋና
እንደ ፡ ሃጥያታችን ፡ አላደረክብን
በበደላችን ፡ መቼ ፡ አጠፋኸን
ከቁጣህ ፡ ምሕረትህ ፡ ትቀድማለች
ለደካከሙት ፡ ብርታት ፡ ትሆናለች
ምሕረትህ ፡ ቸርነትህ
ደግነትህ ፡ ርህራሄህ (፪x)
ወደፊት ፡ እንደርሳለን ፡ በአዳዲስ ፡ ምሥጋና
ከልባችን ፡ በደስታ ፡ ልንሰግድልህ ፡ እንደገና
እያመለክን ፡ ልናመልክህ ፡ እናብዛልህ ፡ ብዙ ፡ ቅኔ
ከሃጥያት ፡ ስለፈታኸን ፡ ስለወጣን ፡ ከኩነኔ (፪x)
እንደገና (፯x)
በአዲስ ፡ ምሥጋና
እንደገና (፯x)
በአዲስ ፡ ምሥጋና
ከጥፋት ፡ የታደከን ፡ ከመከራ
ቸርነትህ ፡ አያልቅም ፡ ብናወራ
ገደብ ፡ የለው ፡ ይቅርታህ ፡ በሕዝብህ ፡ ላይ
ምሕረትህ ፡ ከፍ ፡ ያለች ፡ ናት ፡ እስከ ፡ ሰማይ
ምሕረትህ ፡ ቸርነትህ
ደግነትህ ፡ ርህራሄህ (፬x)
|