From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ልዑል ፡ አምላካችን ፡ እስኪ ፡ እንስገድልህ
የሚያክልህ ፡ የለም ፡ በግርማም ፡ በኃይልህ
ሥልጣናት ፡ አለቆች ፡ ለአንተ ፡ ተገዙ
ውበትህን ፡ አይተው ፡ በግርማህ ፡ ፈዘዙ
አዝ፦ ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አምላካችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ ፈጣሪያችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ለእርስትህ ፡ መረጥከን ፡ ለየኸን
ሕዝቦችህ ፡ አደረግከን ፡ (፪x)
ምድርን ፡ በኃይልህ ፡ የፈጠርክ
ዓለምን ፡ በጥበብህ ፡ መሠረትክ
ሰማያትን ፡ በማስተዋል ፡ የዘረጋህ
አምሳያ ፡ የለህም ፡ ከአንተ ፡ ሚጠጋ(፪x)
አዝ፦ ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አምላካችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ ፈጣሪያችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ለእርስትህ ፡ መረጥከን ፡ ለየኸን
ሕዝቦችህ ፡ አደረግከን ፡ (፪x)
ልዑል ፡ አምላካችን ፡ እስኪ ፡ እንስገድልህ
የሚያክልህ ፡ የለም ፡ በግርማም ፡ በኃይልህ
ሥልጣናት ፡ አለቆች ፡ ለአንተ ፡ ተገዙ
ውበትህን ፡ አይተው ፡ በግርማህ ፡ ፈዘዙ
አዝ፦ ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አምላካችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ ፈጣሪያችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ለእርስትህ ፡ መረጥከን ፡ ለየኸን
ሕዝቦችህ ፡ አደረግከን ፡ (፪x)
ዙፋንህ ፡ ጽኑ ፡ ማይነቃነቅ
ዓመትህ ፡ ተቆጥሮ ፡ የማያልቅ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል ፡ ኃያል ፡ ግሩም ፡ ብርቱ
የጠቢባን ፡ ጥበብ ፡ በፊትህ ፡ ነው ፡ ከንቱ
አዝ፦ ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አምላካችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ ፈጣሪያችን ፡ ነህ
ኦሆ ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
|