አንተ ፡ ተሰበክ (Ante Tesebek) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 2.jpg


(2)

መንግሥትህ ፡ ትምጣ
(Mengesteh Temta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

በእድሜ ጠዋት ልጅ ሳለው አግኝተህ
ተንከባክበህ ያዝከኝ በሚያስደንቅ ትግስትህ
እንዳገለግልህ እድሉን አገኘሁኝ
ስላንተ እንድናገር በህዝብህ ፊት አቆምከኝ

እኔ ልታከብረኝ (ክብርህን ትተሀል) (፪x)
ከሰማይ ሰማያት (ስለኔ ወርደሀል) (፪x)
የማልጠቅም ስሆን ሰው አድርገኸኛል
     ልጅህ አርገኸኛል
በኔ ፈንታ ሞተህ (አስገኝተኸኛል) 2x

ውድዬ አንተ ክበር
ኧረ አንተ ንገሥ
አንተ ከብረህ ታይ በኔ ላይ
አንተ ደምቀሕ ታይ
 
ከመሬት አንስተህ በከፍታ ስፍራ እግሮቼ ሲቆሙ
ጌትነትህ ይግነን ከፍ ከፍ ያድርጉህ ባንተ ይደመሙ
ዛሬ ቀን ከወጣ በህዝብህ ፊት ብቆም በኔ ላይ ብትሰራ
ሰዉ ሁሉ አንተን ይይ በሀገር በምድሩ ስላንተ ይወራ
        
አንተ ተወራ - ክብሬ ነህ
አንተ ተወራ - ድምቀቴ
አንተ ተወራ - ውበቴ
አንተ ተወራ - የኔጌታ
አንተ ከብረህ ታይ በእኔ ላይ
አንተ ነግሰህ ታይ

እኔን ልታከብረኝ ክብርህን ትተሀል ክብርህን ትተሀል
ከሰማይ ሰማያት ስለኔ ወርደሀል በረት ተወልደሃል
የማልጠቅም ሳለሁ ሰው አድርገኸኛል ልጅህ አርገኸኛል
በኔ ፈንታ ሞተህ (አስገኝተኸኛል) [x2]

ውድዬ አንተ ክብር
ኧረ አንተ ከብር
አንተ ድመቅ ኢየሱስ አንተ ድመቅ ጌትዬ
አንተ ክበር ኧረ አንተ ድመቅ

          
በበደሌ ምክንያት የተፈረደብኝ ነበርኩኝ የወደኩ
ጌታዬ አነሳኸኝ ሀጥያቴ ተሽሮ በደምህ ታጠብኩኝ
ባይገባኝ እንኳን ለኔ የሆንከው ነገር ፍቅርን ገልጦልኛል
መርገሜን ወስደህልኝ ውዴ በኔ ፋንታ በአብ ፊት ታይተሀል
   
አንተ ታይልኝ እየሱስ
አንተ ተወራ የኔ ጌታ
አንተ ከብረህ ታይ የሱሴ
አንተ ደምቀህ ታይ ክብሪ ነህ
አንተ ከብረህ ታይ
ኧረ አንተ ደምቀህ ታይ
አንተ ገነሕ ታይ በኔ ላይ
አንተ አምረሕ ታይ