From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ የእኔን ፡ ነገር ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ
የያዘልኝ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከሰማይ (፪x)
ማደሪያው ፡ ልግባና
ላምልከው ፡ አንስቼ ፡ በገና (፪x)
የማማርረው ፡ አልሞላም ፡ ብዬ
ስሙን ፡ ላወድስ ፡ ሀዘኔን ፡ ጥዬ
ቢጐድልም ፡ እንኳን ፡ ወይኑ ፡ በለሱ
በዚህ ፡ አይለካም ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ እርሱ
ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ
ላመስግነው ፡ ሳለይ ፡ ሁኔታ (፪x)
እኔ ፡ አለሁኝ ፡ አለሁኝ ፡ አበዛለው ፡ ብዙ ፡ ምስጋና
ሰው ፡ ሆኛለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱሴ ፡ በሰራው ፡ ስራ
ከትላንቱ ፡ ከአስፈሪው ፡ ከጨለማው ፡ ከዚያ ፡ ግዛት
ያመለጠ ፡ የዳነ ፡ ለጌታዬ ፡ ይስገድለት
አምጡለታ ፡ አምጡለታ
ሲያንስበት ፡ ነው ፡ እልልታ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x)
አዝ፦ የእኔን ፡ ነገር ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ
የያዘልኝ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከሰማይ (፪x)
ማደሪያው ፡ ልግባና
ላምልከው ፡ አንስቼ ፡ በገና (፪x)
የዘላለም ፡ አባት ፡ የመዳኛ ፡ ደግሞም ፡ ካህኔ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አምለኬ ፡ የሆነው ፡ ለእኔ
ከአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ሆኖ ፡ ስለእኔ ፡ እየማለደ
ዛሬም ፡ አለው ፡ በእቅፉ ፡ ጠላቴን ፡ እያዋረደ
አምጡለታ ፡ አምጡለታ
ሲያንስበት ፡ ነው ፡ እልልታ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x)
አዝ፦ የእኔን ፡ ነገር ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ
የያዘልኝ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከሰማይ (፪x)
ማደሪያው ፡ ልግባና
ላምልከው ፡ አንስቼ ፡ በገና (፬x)
|