ተወለድ ፡ እንደገና (Tewelede Endegena) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 1.jpg


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ ሞትን ፡ ለሚጠብቀው
እረፍትን ፡ ፍለጋ ፡ ተቅበዝብዞ ፡ ሰላሙ ፡ ለራቀው
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መፍትሄው
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሚያድነው (፪x)

በራስህ ፡ ኃይልና ፡ ጉልበት ፡ ነፍስህን ፡ አታድንም
በያዝከው ፡ ሃብትና ፡ ንብረት ፡ እርካታን ፡ አታገኝም
ይልቅስ ፡ ቶሎ ፡ ብለህ : ና ፡ ትምክትህን ፡ ተውና
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ብለህ ፡ ተወለድ ፡ እንደገና

ያኔ ፡ ነው ፡ እርካታህ
ያኔ ፡ ነው ፡ ፍፁም ፡ ደስታህ (፪x)

በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ ሞትን ፡ ለሚጠብቀው
እረፍትን ፡ ፍለጋ ፡ ተቅበዝብዞ ፡ ሰላሙ ፡ ለራቀው
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መፍትሄው
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሚያድነው (፪x)

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሲሞት ፡ እዳህን ፡ ተሸክሞ
ከኃጢአት ፡ ደዌ ፡ ሊያድንህ ፡ ስለአንተ ፡ እርሱ ፡ ቆስሎ
ኃጢአትህን ፡ ደምስሶልሃል ፡ ንጹህ ፡ ደሙን ፡ አፍስሶ
ና ፡ ልጄ ፡ ናና ፡ ይልሃል ፡ ስራህንም ፡ ጨርሶ

ድምጹን ፡ ስማ ፡ ወዳጄ ፡ ተከፍቷል ፡ የምህረት ፡ ደጄ
ድምጹን ፡ ስማ ፡ ወዳጄ ፡ ተከፍቷል ፡ የምህረት ፡ ደጄ

በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ ሞትን ፡ ለሚጠብቀው
እረፍትን ፡ ፍለጋ ፡ ተቅበዝብዞ ፡ ሰላሙ ፡ ለራቀው
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መፍትሄው
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሚያድነው (፪x)