Meskerem Getu/Eketelehalehu/Temechetogn New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search


ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅርህ ተመችቶኝ ነው (፬x)
ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x)

ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ
ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ
ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ
አለሁኝ የምትል ለተጐዳ

አዝ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x)

ከወረት ያልሆነ ታላቅ ፍቅርህ
ሀዘኔን የሚያልፍ መፅናናትህ
እምባዬን ያበሰከው ደጋፊዬ
ስተክዝ ሆንክልኝ መፅናኛዬ

አዝ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x)

አትከዳኝ አትለወጥ በሁኔታ
አተወኝ ስደክም ስበረታ
ፍቅርህ የፍቅሮች ሁሉ አውራ
ዘለዓለም የሚቀጥል እያበራ

አዝ ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅር ተመችቶኝ ነው (፬x)
ከአንተ ጋራ መዋል ማደሩ ከአንተ ጋራ (፪x)

ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ (ከአንተ ጋራ)
ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ (ከአንተ ጋራ)
ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ (ከአንተ ጋራ)
አለሁኝ የምትል ለተጐዳ (ከአንተ ጋራ) (፪x)