ለእኔ ፡ መሞቱን (Lenie Memotun) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 1.jpg


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ተስፋ ፡ ሰጥቶኝ ፡ ሄደ ፡ የርስቴን ፡ መያዣ
መንፈሱን ፡ ላከልኝ ፡ ለሕይወቴ ፡ ማደሻ
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ማግኛ ፡ መንገዱን
አሳይቶኝ ፡ ሄዷል ፡ ለእኔ ፡ መሞቱን

አዝ፦ ለእኔ ፡ መሞቱን ፤ ለእኔ ፡ መሞቱን (፬x)

በምድር ፡ እስካለሁ ፡ እስካሁን ፡ ድረስ
ሳዝን ፡ የሚያበረታኝ ፡ እምባዬን ፡ ሚያብስ
በርስቴ ፡ መያዣ ፡ በታተምኩበት
ዘለዓለም ፡ እኖራለሁ ፡ በእርሱ ፡ መጽናናት

አዝ፦ ለእኔ ፡ መሞቱን ፤ ለእኔ ፡ መሞቱን (፬x)

አሁን ፡ አውቄያለሁ ፡ የሚረባኝን
በኑሮዬ ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ መሾም ፡ ያለብኝን
የእኔ ፡ መጀመሪያ ፡ ብሎም ፡ መጨረሺያዬ
ከምንም ፡ ከማንም ፡ በላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x)

ዘላቂ ፡ ላልሆነው ፡ ለጊዜያዊው ፡ ደስታ
እራሴን ፡ አላቀርብም ፡ ለሚያልቀው ፡ በዋይታ
በመጠበቂያዬ ፡ ላይ ፡ እርሱን ፡ እጠብቃለሁ
አይቀርም ፡ ይመጣል ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ

አዝ፦ ለእኔ ፡ መሞቱን ፤ ለእኔ ፡ መሞቱን (፬x)

አሁን ፡ አውቄያለሁ ፡ የሚረባኝን
በኑሮዬ ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ መሾም ፡ ያለብኝን
የእኔ ፡ መጀመሪያ ፡ ብሎም ፡ መጨረሺያዬ
ከምንም ፡ ከማንም ፡ በላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x)