ላይተወኝ ፡ ቃል ፡ ገብቶአል (Laytewegn Qal Gebtual) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 1.jpg


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ያላዩት ፡ አገር ፡ አይናፍቅም ፡ እንደሚሉት ፡ ሰዎች
ተረት ፡ አይደለም ፡ ዓይኔ ፡ አይቶት ፡ ነው ፡ የልቦናዬ
ሕይወቴን ፡ እንካ ፡ ኑሮዬን ፡ እንካ ፡ ብዬ ፡ የሰጠሁት ፡ ለዚህ ፡ ጌታዬ

ዛሬም ፡ ፍቅሩ ፡ ያዘኝ
ምህረቱ ፡ ያዘኝ
ፀጋው ፡ ያዘኝ
ያዘኝ (፭x)
ያዘኝ (፬x)

ላይተወኝ ፡ ቃል ፡ ገብቷል ፡ ላይጥለኝ
የጌታዬ ፡ ፍቅሩ ፡ ማረከኝ (፪x)

ሰላሙን ፡ ሞላ ፡ በቤቴ
ተለወጠልኝ ፡ ሕይወቴ
በቀኙ ፡ ደግፎ ፡ ያዘኝ
መንፈሱ ፡ አሳረፈኝ

አሁን ፡ አሁንማ (አሁንማ)
ለሌላው ፡ አተረፈኝ
ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ (፪x)

ልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ሆነኝ ፡ በክንፉ ፡ አሳረፈኝ
ልቤ ፡ ከሥጋት ፡ አረፈ ፡ ጽዋዬ ፡ እየተረፈ (፪x)

አሁን ፡ አሁንማ (አሁንማ)
ለሌላው ፡ አተረፈኝ
ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ (፪x)

በጠላቶቼ ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ቀባኝ ፡ አምላኬ ፡ በዘይት
ገመዴ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀች/ወድቃለች ፡ ልቤ ፡ እንዳይፈራ (፪x)

አሁን ፡ አሁንማ (አሁንማ)
ለሌላው ፡ አተረፈኝ
ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ (፪x)