ሕይወቴን ፡ ፈውስ (Hiwotien Fewes) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 1.jpg


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ብላቴና ፡ ሳለሁ ፡ የመረጥከኝ ፡ አምላክ
ለአንተ ፡ እንድዘምር ፡ ታማኝ ፡ አርገህ ፡ ቆጥረህ
በሁለንተናዬ ፡ እንዳከብርህ ፡ አንተን
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ፈውሰው ፡ ሕይወቴን

አዝእባክህ ፡ ኢየሱስ (፪x) ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ/ቀይር
ሰዎች ፡ እኔን ፡ ሲያዩ ፡ ስምህ ፡ እንዲቀደስ/እንዲከበር (፪x)

እባክህ ፡ ባክህ ፡ እግዚአብሔር
ሕይወቴን ፡ ቀይር
ሕይወቴን ፡ ቀይር
እባክህ

ሕዝብህን ፡ ልትባርከው ፡ ስትሰጠኝ ፡ ፀጋ
ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ
ለታይታ ፡ አይሁን ፡ መንፈሳዊነቴ
አንተን ፡ እንዲገልጥህ ፡ መላው ፡ እኔነቴ

አዝኢየሱስ ፡ አባቴ (፪x) ፡ ክበር ፡ በሕይወቴ
በሁሉ ፡ ይገለጥ ፡ የሕይወት ፡ እድገቴ

ስለእኔ ፡ ኃጢአት ፡ ደምህ ፡ ፈሶልኛል
እራስህን ፡ ሰውተህ ፡ ሕያው ፡ አድርገኸኛል
እኔ ፡ ግን ፡ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ተስኖኛል
እጅህ ፡ ግን ፡ ከመጣ ፡ አድኖ ፡ ያስቀረኛል

አዝእባክህ ፡ ኢየሱስ (፪x) ፡ ሕይወቴን ፡ ቀድስ
አንተን ፡ ለተራቡ ፡ ቃልህን ፡ እንዳለ

ሕያውና ፡ ቅዱስ ፡ መስዋዕት ፡ አድርጌ
ለአንተ ፡ ሰውነቴን ፡ እንዳቀርብ ፡ አምላኬ
በፍፁም ፡ መለወጥ ፡ ሕይወቴ ፡ ይገራ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ እንድፈራ

አዝእባክህ ፡ እግዚአብሔር (፪x) ፡ ሕይወቴን ፡ ቀይር
ደግሞም ፡ መጨረሻዬ ፡ በፊትህ ፡ እንዲያምር (፪x)