From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ለእኔ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ (፪x)
መሞት ፡ የሚገባኝ ፡ ነበርኩ
መጣልኝ ፡ ሲሳይ
አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር
ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ
እንደዚህ ፡ የሚያደርገው
ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x)
ከላይ ፡ ከሰማይ ፡ የባሪያን ፡ መልክ ፡ ይዞ
በእኔ ፡ በኃጢአተኛዋ ፡ በፍቅር ፡ ተይዞ
ካለሁበት: አዘቅት፡ ከሞት ፡ ሊያወጣኝ
እርሱ ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ነጻ ፡ ነሽ ፡ አለኝ
አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር
ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ
እንደዚህ ፡ የሚያደርገው
ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x)
በዚያ ፡ በጐልጐታ ፡ በቀራኒዮ ፡ ላይ
ከቶ ፡ መች ፡ አፈረ ፡ እርቃኑ ፡ ሲታይ
የህማም ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ ተመታ ፡ በደዌ
እርሱ ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ይኸው ፡ ዳንኩኝ
አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር
ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ
እንደዚህ ፡ የሚያደርገው
ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x)
ወርዱና ፡ ስፋቱ ፡ የማይለካው
ጥልቅ ፡ ነው ፡ ፍቅሩ ፡ ወሰን ፡ የሌለው
የልቤ ፡ አይወጣም ፡ ብዙ ፡ ቃል ፡ ደርድሬ
ሳመሰግን ፡ ብውል ፡ በመልካም ፡ ዝማሬ
ለእኔ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ (፪x)
መሞት ፡ የሚገባኝ ፡ ነበርኩ
መጣልኝ ፡ ሲሳይ
አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር
ፍቅር ፡ ነው ፡ ለእኔ
እንደዚህ ፡ የሚያደርገው
ከእኔ ፡ ምንም/አንዳች ፡ የለ (፪x)
|