እከተልሃለሁ (Eketelehalehu) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

አዝ፦ የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ከፊቴ ፡ ሁን ፡ አንተ
እከተልሃለሁ ፡ አታውቅም ፡ ተሳስተህ
ከአንተ ፡ እየተማርኩ ፡ ሕይወቴ ፡ ይገራ
ጭምተኛ ፡ ልሁን ፡ እንድመስልህ ፡ ልትጋ

እከተልሃለሁ ፡ (ጌታ) ፡ እከተልሃለሁ ፡ (ኦ)
ከአንተ ፡ ትህትናን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የምማረው
እከተልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ እከተልሃለሁ
ከአንተ ፡ ቅድስና ፡ (ቅድስና)
ብዙ ፡ ነው ፡ የምማረው

ትልቅ ፡ ሆነህ ፡ ሳለህ ፡ ከሁሉ ፡ የምትበልጥ
ደቀ ፡ መዘሙርቱን ፡ እግራቸውን ፡ አጠብክ
ትዕቢተኝነትን ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ አላየሁ
ራስን ፡ ዝቅ ፡ ማድረግ ፡ ከአንተ ፡ እማራለሁ

አዝ፦ የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ከፊቴ ፡ ሁን ፡ አንተ
እከተልሃለሁ ፡ አታውቅም ፡ ተሳስተህ
ከአንተ ፡ እየተማርኩ ፡ ሕይወቴ ፡ ይገራ
ጭምተኛ ፡ ልሁን ፡ እንድመስልህ ፡ ልትጋ

እከተልሃለሁ ፡ (ጌታ) ፡ እከተልሃለሁ ፡ (ኦ)
ከአንተ ፡ ትህትናን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የምማረው
እከተልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ እከተልሃለሁ
ከአንተ ፡ ቅድስና ፡ (ቅድስና)
ብዙ ፡ ነው ፡ የምማረው

የሥጋዊ ፡ ነገር ፡ ማልመድ ፡ ሰውነትን
ለጥቂት ፡ ይጠቅማል ፡ ይሰጣል ፡ ጊዜያዊ ፡ ደስታ
ግን ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ መምሰል ፡ የዘለዓለሙን
እጅግ ፡ ተስፋ ፡ አለው ፡ መከተል ፡ አንተን (፪x)

አዝ፦ የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ከፊቴ ፡ ሁን ፡ አንተ
እከተልሃለሁ ፡ አታውቅም ፡ ተሳስተህ
ከአንተ ፡ እየተማርኩ ፡ ሕይወቴ ፡ ይገራ
ጭምተኛ ፡ ልሁን ፡ እንድመስልህ ፡ ልትጋ

እከተልሃለሁ ፡ (ጌታ) ፡ እከተልሃለሁ ፡ (ኦ)
ከአንተ ፡ ትህትናን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የምማረው
እከተልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ እከተልሃለሁ
ከአንተ ፡ ቅድስና ፡ (ቅድስና)
ብዙ ፡ ነው ፡ የምማረው