አይዞህ (Ayzoh) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ነገን ፡ ነገን ፡ ስታይ ፡ ቢጨልምብህ/ከጨልምብህ
በተስፋ ፡ ተራመድ ፡ እራዕይ ፡ ይኑርህ/አለህ (፪x)

አይዞህ (፫x)
ሥራ ፡ ብታጣ ፡ ገንዘብ ፡ ቢጠፋ
ቢጨልምብህ ፡ አይዞህ
ሚረዳህ ፡ አጥተህ ፡ ብቻህን ፡ ብትሆን
ተስፋ ፡ ባይኖርህ ፡ አይዞህ (፪x)

አስሩን ፡ ስታስብ ፡ ሚሰማህ ፡ እንዳነስህ
ከሁሉ ፡ የበታች ፡ የሆንክ ፡ የመሰለህ

አይዞህ (፫x)
ልዩ ፡ የሆነ ፡ ችሎታ ፡ አለህ
ተነስ ፡ ታገል ፡ አይዞህ
ከማንም ፡ አታንስ ፡ ይኸው ፡ ራስህም
ብቃት ፡ እኮ ፡ አለህ ፡ አይዞህ

መስራት ፡ ማችልበት ፡ ምንም ፡ ምክኒያት ፡ የለ
ጠንክረህ ፡ ብትሰራ ፡ ብዙ ፡ ታጭዳለህ

አይዞህ (፫x)
የረፈደብህ ፡ እየመሰልህ
ትተክዛለህ ፡ አይዞህ
በዚህ ፡ ጉብዝናህ ፡ በሙሉ ፡ ኃይልህ
መራመድ ፡ ጀምር ፡ አይዞህ

አንድ ፡ ቀን ፡ ያልፋል (፫x)
የወደደ ፡ ያከበረ ፡ ያፈቀረ
አምላክ ፡ አለህ ፡ አለህ
የወደደ ፡ ያፈቀረ ፡ ያከበረ
አምላክ ፡ አለህ ፡ አለህ