አማኑኤል (Amanuel) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 1.jpg


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

በለጋነት ፡ ልቤ ፡ ፍቅርህ ፡ አሸንፎኛል
ከአንተ ፡ የትም ፡ አልሄድም
አንተ ፡ ተመችተኸኛል

ቃላትም ፡ የማይገልጹት ፡ ሰማያዊ ፡ ደስታ
በህይወት ፡ መመስከር ፡ መገዛት ፡ ለጌታ
እኔ ፡ ለብቻዬ ፡ ስሆን ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ
የአባትነቱን ፡ ፍቅር ፡ ቀምሻለሁ

ጌታን ፡ አውቀዋለሁ
ጌታን ፡ አመልካለሁ
ለጌታ ፡ እገዛለሁ
ጌታን ፡ እወደዋለሁ

ኢየሱሴ ፡ አንተን ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልግለጽህ
ቃላቶች ፡ አነሱ ፡ በምን ፡ ልተርክህ
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ማውቀው ፡ የሚደንቅ ፡ ነገር
እጅጉን ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ከአንተ ፡ ሲወዳደር

አማኑኤል (አማኑኤል) ፤ አማኑኤል
አማኑኤል (ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው)
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
እግዚአብሔር
(እግዚአብሔር)

አባት ፡ ለልጆቹ ፡ ሃይማኖት ፡ ያወርሳል
ልጅ ፡ የተማረውን ፡ ስርዓት ፡ ይፈጽማል
ግን ፡ የጌታን ፡ ፍቅር ፡ አላስተዋለውም
ሃይማኖቱን ፡ እንጂ ፡ ጌታን ፡ ከቶ ፡ አልተቀበለም

ጌታዬ ፡ ግን ፡ ድኅነት
ለሚሹህ ፡ ቅርብ ፡ ነህ
አንተ ፡ ትሻሃላለህ
አንተ ፡ ታዋጣለህ

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ ተረድቼሃለሁ
በወረስኩት ፡ ሳይሆን ፡ በግሌ ፡ አውቅሃለሁ
ከቤትህ ፡ ርቄ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል ፡ አንተን ፡ መርጫለሁ

አማኑኤል (አማኑኤል) ፤ አማኑኤል
አማኑኤል (ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው)
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
እግዚአብሔር
(እግዚአብሔር)