አማላጄ (Amalajie) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

Meskerem Getu 1.jpg


(1)

እከተልሃለሁ
(Eketelehalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 3:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

በቅድሚያ ፡ ነብያት ፡ የተናገሩለት
ስለእርሱ ፡ ሚያወራ ፡ መጽሐፉ ፡ ቢገለጥ
እግዚአብሔርም ፡ አለ ፡ ልጄ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ስሙት
እናቱ ፡ ማርያምም ፡ ሚላችሁን ፡ አድምጡ

አዝ፦ አማላጄ ፡ ኢየሱሴ ፡ ነው (፬x)
ኢየሱሴ ፡ ነው ፤ ኢየሱሴ ፡ ነው (፬x)

ሌሎች ፡ ፍጥረታቶች ፡ አማላጅ ፡ ሚባሉ
እስቲ ፡ እንያቸው ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ከዋሉ
በቀራኒዮ ፡ መስቀል ፡ የሞተው ፡ ስለእኛ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ መዳኛ

አዝ፦ አማላጄ ፡ ኢየሱሴ ፡ ነው (፬x)
ኢየሱሴ ፡ ነው ፤ ኢየሱሴ ፡ ነው (፪x)

እውነትና ፡ ሕይወት ፡ ሰላም ፡ መንገድ ፡ ነኝ ፡ ያለው
በእርሱ ፡ በቀር ፡ ወደአብ ፡ ሚሄድ ፡ ኧረ ፡ እስቲ ፡ ማነው
እግዚአብሔር ፡ አብ ፡ የሰውን ፡ ልጅ ፡ ይጠራዋልና
በሚያድነው ፡ በኢየሱስ ፡ ይዳን ፡ ይመንና
ይዳን ፡ ይመንና (፬x)

በቅድሚያ ፡ ነብያት ፡ የተናገሩለት
ስለእርሱ ፡ ሚያወራ ፡ መጽሐፉ ፡ ቢገለጥ
እግዚአብሔርም ፡ አለ ፡ ልጄ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ስሙት
እናቱ ፡ ማርያምም ፡ ሚላችሁን ፡ አድምጡ

አዝ፦ አማላጄ ፡ ኢየሱሴ ፡ ነው (፬x)
ኢየሱሴ ፡ ነው ፤ ኢየሱሴ ፡ ነው (፬x)