ዙፋኑ ፡ ላይ (Zufanu Lay) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ
የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ
ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ
ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ
ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x)

በደሌ ፡ እንደሙታን ፡ አድንዞኝ ፡ ሳለሁ
በኢየሱሴ ፡ በኩል ፡ ወደአብ ፡ ዘንድ ፡ ገባሁ
በሥጋዬ ፡ ምኞት ፡ እየኖርኩኝ ፡ ሳለሁ
ከፍቅሩ ፡ የተነሳ ፡ ፀጋውን ፡ አገኘሁ

አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ
የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ
ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ
ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ
ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x)

ቸርነቱን ፡ ሊያሳይ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አስነሳኝ
በላይኛው ፡ ስፍራ ፡ በቀኙ ፡ አስቀመጠኝ
እንግዲህ ፡ አልመካም ፡ ከስራዬ ፡ አይደለም
በእምነት ፡ የተገኘ ፡ ስጦታ ፡ ነው ፡ ይኸው

አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ
የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ
ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ
ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ
ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x)

ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ አደንቅሃለሁ
በአንተ ፡ ውብ ፡ ፍቅር ፡ ተነድፌያለሁኝ (፪x)

አዝ፦ ዓይኖቼ ፡ አይተውህ ፡ እጅጉን ፡ ፈዘዙ
የፍቅርን ፡ እንባ ፡ አወጡ ፡ ከቶ ፡ ሳይታዘዙ
ነፍሴም ፡ አልቻለችም ፡ መድሃኒቷን ፡ ስታይ
ከጐኑ ፡ ስትሆን ፡ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ
ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ዙፋኑ ፡ ላይ ፤ ከዚያ ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ (፪x)