መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል (Mechie Zem Yasegnal) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

ምሥጋና ፡ ይሞላ ፡ ሁልጊዜ ፡ አንደበቴ
ለጸሎት ፡ ይንበርከክ ፡ እስኪዝል ፡ ጉልበቴ
አፌም ፡ ይንቀሳቀስ ፡ ያውራ ፡ ስራህን
ምላሴም ፡ ይናገር ፡ ይበል ፡ ክብርህን
(፪x)

አዝ፦ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታህ
ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ (፪x)

አጽናናህ ፡ አበረታህ ፡ ቁርጭምጪሚቴን
እየሮጥኩኝ ፡ ላውራ ፡ ሜዳ ፡ ዳገቱን
ይህ ፡ የመዳን ፡ ወንጌል ፡ ለዓለም ፡ ይዳረስ
በሠማያዊው ፡ ጠል ፡ ነፍስ ፡ ሁሉ ፡ ይረስርስ
(፪x)

አዝ፦ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታህ
ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ (፪x)

ላላወቁህ ፡ ሁሉ ፡ ቀርበው ፡ ላልቀመሱ
መናገር ፡ እንድችል ፡ ሙላኝ ፡ በመንፈስህ
ሕይወቴ ፡ አርክቶህ ፡ ወዳንተ ፡ እስክደርስ
ምስክር ፡ አድርገህ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ
(፪x)

አዝ፦ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታህ
ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራትህ (፪x)