ክብሩን ፡ ሳየው (Keberun Sayew) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

ከእንግዲህ ፡ ለማን ፡ ብዬ ፡ ለምን ፡ ብዬ
አልሳሳም ፡ ለሕይወቴ ፡ ተስገብግቤ
ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ ክርስቶስ ፡ እንደሆነ ፡ አውቃለሁ
እራሴንም ፡ እንደመስዋዕት ፡ ፉቱ ፡ አቀርባለሁ (፪x)

ለእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ (ለእግዚአብሔር ፡ ነው)
ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ የማይቆጨኝ (የማይቆጨኝ) ፡ ብሰዋለት
ለእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ (ለእግዚአብሔር ፡ ነው)
ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ የማይቆጨኝ ፡ ብሰዋለት

ዓይኖቼ ፡ በርተውልኝ ፡ ጌታን ፡ ሳየው
ቸርነቱን ፡ ቀምሼ ፡ ሳጣጥመው
ሌላው ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ይደበዝዝና
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ይሆናል ፡ ልቤን ፡ የሚሞላ (፪x)

ክብሩን ፡ ሳየው ፡ (ክብሩን ፡ ሳየው)
ግርማውን ፡ ያስጥለኛል ፡ (ያስጥለኛል) ፡ ሁሉንም
ክብሩን ፡ ሳየው ፡ (ክብሩን ፡ ሳየው)
ግርማውን ፡ ያስጥለኛል ፡ ሁሉንም

ክብሩን ፡ ሳይሆን ፡ ሞቱን ፡ የተመኙ
የሄደበትን ፡ መንገድ ፡ ተረድተውት
ማቄን ፡ ጨርቄን ፡ ሳይሉ ፡ ሁሉንም ፡ ወርውረው
እርሱን ፡ እርሱን ፡ ያሉት ፡ ከቶ ፡ ለምንድን ፡ ነው (፪x)

ያ ፡ ፍቅሩ ፡ ነው ፡ (ያ ፡ ፍቅሩ ፡ ነው)
የሚያስጥለው ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ (ሌላ ፡ ነገር) ፡ የማያስመኘው ፡ ነው
ሊያፈቅሩ ፡ ነው ፡ (ሊያፈቅሩ ፡ ነው)
የሚያስጥለው ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ (ሌላ ፡ ነገር) ፡ አያስመኝም

ለእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ (ለእግዚአብሔር ፡ ነው)
ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ የማይቆጨኝ ፡ (የማይቆጨኝ) ፡ ብሰዋለት
ክብሩን ፡ ሳየው ፡ ግርማውን
ያስጥለኛል ፡ (ያስጥለኛል) ፡ ሁሉንም