ክብር ፡ ያስመለሱ (Keber Yasmelesu) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

ክብር ፡ ያስመለሱ ፡ መሰውያን ፡ ያደሱ
ሁሉም ፡ የረሱትን ፡ በእድሜያቸው ፡ ያነሱ
እግዚአብሔርን ፡ ሽተው ፡ ታሪክ ፡ ያስለወጡ
በየዘመናቸው ፡ ለእውነት ፡ የተሰጡ
ነበሩ ፡ አምላካቸውን ፡ ፈገግ ፡ ያስደረጉ
ከእጁ ፡ ይልቅ ፡ ፊቱን ፡ ለልብ/ከምር ፡ የፈለጉ
(፪x)

በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ሌላ ፡ አልሻም
አንተን ፡ እንጂ ፡ ጌታ ፡ ሌላ ፡ አላሳድድም
በልቤም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ አይቀመጥም
ለአንተ ፡ እንጂ ፡ አምላኬ ፡ ለማንም ፡ አይሆንም

ብዙዎች ፡ ረክተዋል ፡ የእጅህን ፡ ስራ ፡ አይተው
እንጀራም ፡ ተርበው ፡ ስላበላሃቸው
በከንቱ ፡ ፈለጉህ ፡ ደግመህ ፡ እንድጸጣቸው
በቃኝ ፡ በማያውቀው ፡ ከንቱ ፡ መሻታቸው
እኔ ፡ ግን ፡ አንዲት ፡ ነገር ፡ እለምንሃለሁ
ከምትሰጠኝ ፡ በላይ ፡ አንተኑ ፡ እሻለሁ
(፪x)

ወደቀኝም ፡ ሳልል ፡ ወደግራም ፡ ሳላይ
የመደበልኝን ፡ ተቀብዬ ፡ ከላይ
ሩጫዬን ፡ እሮጣለሁ ፡ እርሱ ፡ እየመራኝ
በመጨረሻው ፡ ቀን ፡ በእጣ ፡ ክፍሌ ፡ እንድገኝ
ወሰንኩኝ ፡ ላልመለስ ፡ እስከመጨረሻ
ከአምላኬ ፡ በስተቀር ፡ ልቤም ፡ ሌላ ፡ አይሻ
(፬x)