ጌታን ፡ ልባርከው (Gietan Lebarkew) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

ኑሮ ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ የያዝኩት
ሕይወት ፡ ብዬ ፡ የመረጥኩት
የሚተካ ፡ ያልተገኘለት
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የሰጠኝ ፡ እረፍት (፪x)

አዝ፦ ከእርሱ ፡ ሌላም ፡ አልፈልግም
ሌላውም ፡ አልሞተልኝም
ያለኝን ፡ ሁሉ ፡ ብሰጠው
አይቆጨኝ ፡ ለእርሱ ፡ ባፈሰው
እስቲ ፡ ልባርከው ፣ እስቲ ፡ ልባርከው (፬x)

አለኝ ፡ ብዬ ፡ የምኮራበት
በታች ፡ አለው ፡ እኔን ፡ የሚያስንቅ
በብር ፡ በወርቅ ፡ የማይለወጥ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሰላም ፡ የሚሰጥ (፪x)

አዝ፦ ልቤ ፡ ሚሻው ፡ የተጠማው
የማወጣው ፡ የማወርደው
መገኘቱ ፡ የሚናፍቀው
ሌላ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እስቲ ፡ ልባርከው ፣ እስቲ ፡ ልባርከው (፬x)

ከአምላኬ ፡ ጋር ፡ ውዬ ፡ ባድር
የሚመረር. (1) . ፡ አንዳች ፡ ነገር
ሌላ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር
ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር
ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ጌታን ፡ ልባርከው ፡ ጌታን ፡ ልባርከው (፬x)