እኔም ፡ እፊትህ (Eniem Efiteh) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

ክብርህን ፡ ያዩ ፡ ወደው ፡ የተገዙ
ከመንፈስ ፡ ውኃ ፡ በ. (1) . ፡ የጠገ
ከዓለም ፡ ተለዩ ፡ አንተን ፡ ወደዱ
የሙጥኝ ፡ ብለው ፡ ግርማህን ፡ አዩ

አዝ፦ እኔም ፡ እፊትህ ፡ ዛሬ ፡ እወድቃለሁ
ክብርህን ፡ ሳላይ ፡ መቼ ፡ እነሳለሁ
ተጠማሁ ፡ ጌታ ፡ ሙሉ ፡ ግርማህን
ጆሮ ፡ ያልሰማውን ፡ ዓይንም ፡ ያላየውን (፪x)

ቃልህን ፡ በግልጥ ፡ እንዲናገሩ
ተሰበሰቡ ፡ አንተን ፡ ሊጠሩ
ክብርህም ፡ ወርዶ ፡ አንደበት ፡ ነካ
የመገለጥ ፡ ቃል ፡ አፋቸው ፡ ሞላ

አዝ፦ እኔም ፡ እፊትህ ፡ ዛሬ ፡ እወድቃለሁ
ክብርህን ፡ ሳላይ ፡ መቼ ፡ እነሳለሁ
ተጠማሁ ፡ ጌታ ፡ ሙሉ ፡ ግርማህን
ጆሮ ፡ ያልሰማውን ፡ ዓይንም ፡ ያላየውን (፪x)

ያላስተዋልኩት ፡ ከቶ ፡ ያላየሁት
ድካሜ ፡ ይውጣ ፡ በሠማይ ፡ እሳት
ልትሰራ ፡ ጌታ ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ
ይውረድ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ደመናህ ፡ ከላይ

አዝ፦ እኔም ፡ እፊትህ ፡ ዛሬ ፡ እወድቃለሁ
ክብርህን ፡ ሳላይ ፡ መቼ ፡ እነሳለሁ
ተጠማሁ ፡ ጌታ ፡ ሙሉ ፡ ግርማህን
ጆሮ ፡ ያልሰማውን ፡ ዓይንም ፡ ያላየውን (፪x)

ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ፊትህ ፡ እወድቃለሁ
ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እዋረዳለሁ
ደግሞም ፡ ኢየሱስ ፡ እንደነበረ
ትሁት ፡ አገልጋይ ፡ የተሰበረ

አዝ፦ እኔም ፡ እፊትህ ፡ ዛሬ ፡ እወድቃለሁ
ክብርህን ፡ ሳላይ ፡ መቼ ፡ እነሳለሁ
ተጠማሁ ፡ ጌታ ፡ ሙሉ ፡ ግርማህን
ጆሮ ፡ ያልሰማውን ፡ ዓይንም ፡ ያላየውን (፪x)