From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ጽዋ ፡ ሲሞላ ፡ ሰዓቱ ፡ ሲደርስ
የጌታ ፡ ሞገስ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲፈስ
ከፍታውም ፡ ዝቅ ፡ ሸለቆውም ፡ ከፍ
ካለ ፡ በኋላ ፡ ጌታ ፡ ይላል ፡ ከተፍ (፪x)
አዝ፦ በራሱ ፡ ምሎ ፡ በገዛ ፡ ክንዱ
ጣልቃ ፡ የሚገባ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ እርሱ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ቀን ፡ የሚቀጥረው
ያልተጠበቀን ፡ ነገር ፡ የሚያደርገው (፪x)
ገና ፡ ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፪x)
እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ መሆኑን ፡ አይቼ
እጮሃለሁኝ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
የማላቀውን ፡ ነገር ፡ የሚያሳየኝ
እንደእግዚአብሔር ፡ ኧረ ፡ የት ፡ ሊገኝ (፪x)
አዝ፦ በራሱ ፡ ምሎ ፡ በገዛ ፡ ክንዱ
ጣልቃ ፡ የሚገባ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ እርሱ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ቀን ፡ የሚቀጥረው
ያልተጠበቀን ፡ ነገር ፡ የሚያደርገው (፪x)
ገና ፡ ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፪x)
ጌታ ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ነውና
ስለቤቱ ፡ የሚቀና
ቃል ፡ የገባውን ፡ ይፈጽማል
ተስፋውንስ ፡ መቼ ፡ ያጥፋል (፫x)
ገና ፡ ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፪x)
ገና ፡ ብዙ ፡ አለ (ብዙ ፡ አለ)
ብዙ ፡ አለ ፡ (ብዙ ፡ አለ)
ብዙ ፡ አለ ፡ በመዝገቡ (፬x)
|