አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ (Amen Amen Beyie) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

 
ያበጃጁኝ ፡ እጆችህ ፡ እንዴት ፡ የተዋቡ ፡ ናቸው
የደሙትም ፡ እጆችህ ፡ እኔንም ፡ ያቀፉ ፡ ናቸው
ዛሬም ፡ መጥተህ ፡ በእኔ ፡ ላይ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ጫናቸው
(፪x)

የማይጠገብ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ መገኘት
እንደ ፡ ወንዝ ፡ የሚፈስ ፡ አለበት ፡ በእርግጥ (፪x)

አዝ፦ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እሰግዳለሁ
ላከበርከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ
አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እሰግዳለሁ
ላከበርከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ

አንተ ፡ ከነካኸኝ ፡ ምን ፡ ይቀርብኛል
ክብርህ ፡ ይህን ፡ ልቤን ፡ ፈጽሞ ፡ ያጠግባል (፪x)

አዝ፦ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ
ለወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ
አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ
ለወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ

አንተ ፡ ስትጭንብኝ ፡ ሙሉ ፡ ሰው ፡ እሆናለሁ
እስራቴ ፡ ሁሉ ፡ ጠፍቶ ፡ አገኛለሁ
በነካኸኝ ፡ ጊዜ ፡ ጉልበቶቼ ፡ ጸኑ
በረታሁ ፡ በክብርህ ፡ ወጣሁኝ ፡ ዳገቱን

አዝ፦ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ፊትህ ፡ እደፋለሁ
ለመረጥከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ
አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ፊትህ ፡ እደፋለሁ
ለመረጥከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ

ያበጃጁኝ ፡ እጆችህ ፡ እንዴት ፡ የተዋቡ ፡ ናቸው
የደሙትም ፡ እጆችህ ፡ እኔንም ፡ ያቀፉ ፡ ናቸው
ዛሬም ፡ መጥተህ ፡ በእኔ ፡ ላይ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ጫናቸው
(፪x)