አልወጣም ፡ ከፊትህ (Alwetam Kefiteh) - መሥፍን ፡ ማሞ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሥፍን ፡ ማሞ
(Mesfin Mamo)

Mesfin Mamo 1.jpeg


(1)

ሽልማቴ ፡ ነህ
(Shilimateh Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሥፍን ፡ ማሞ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Mamo)

ድምጹን ፡ እያሰማ ፡ ቀኔን ፡ የሚያበራ ፡ አላውቅም ፡ እንደጌታ
መጪውንም ፡ ዘመን ፡ ቀድሞ ፡ የሚናገር ፡ አላየሁም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር
ለዘመኔ ፡ ባዳ ፡ እንዳልሆን ፡ እንግዳ ፡ ሚስጢሩን ፡ ይገልጸዋል ፡ በጓዳ
አምላኬ ፡ ኦ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x)

አዝ፦ አልወጣም ፡ ከፊትህ (ከፊትህ) ፡ አይለየኝ ፡ መንፈስህ (መንፈስህ)
አላማዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ
ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
(፪x)

ድምጽህን ፡ ሰምቼ ፡ እረፍት ፡ ተሞልቼ ፡ ኖሬያለሁ ፡ ጸንቼ
ከአንተ ፡ ተጠግቼ ፡ ልብህን ፡ አግኝቼ ፡ ቀረሁኝ ፡ ገብቼ
ፊትህ ፡ እቆማለሁ ፡ ኃይልህን ፡ አያለሁ
አልወጣም ፡ ከክብርህ ፡ ውስጥ ፡ ወስኛለሁ
አምላኬ ፡ ሆ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x)

አዝ፦ አልወጣም ፡ ከፊትህ (ከፊትህ) ፡ አይለየኝ ፡ መንፈስህ (መንፈስህ)
አላማዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ
ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
(፪x)

እኔስ ፡ አውቄያለሁ ፡ ሚስጥሩን ፡ አግኝቻለሁ
ከመንፈስህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
መነሻ ፡ መድረሻም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ብያለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ጌታ ፡ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ፡ ሆ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x)

አዝ፦ አልወጣም ፡ ከፊትህ (ከፊትህ) ፡ አይለየኝ ፡ መንፈስህ (መንፈስህ)
አላማዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ
ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
(፪x)

አልወጣም ፡ ከፊትህ
አልወጣም ፡ ከፊትህ (አልወጣም ፡ ከፊትህ) (፫x)
ከማደሪያህ ፡ ከመቅደስህ
አልወጣም ፡ ከፊትህ