Mesfin Gutu/Selam New/Yemot Awaj

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ርዕስ የሞት አዋጅ ዘማሪ መስፍን ጉቱ እና ቴዎድሮስ ታደሰ አልበም ሰላም ነው አዝ የሞት አዋጅ አይሰራም በሕይወቴ አይሆንም በሕይወቴ ገልብጦታል ነገሩን አባቴ የሞት አዋጅ አይሰራም በሕይወቴ አይሆንም በሕይወቴ ገልብጦታል ኢየሱስ አባቴ

የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሳ አንበሳ (፪x) ዙሪያ ዙሪያዬን ቢያንዣብብ ሰላሜን ደርሶ ሊነሳ (፪x) መጣ ከሰማይ ወረደ ነደደ የአምላኬ ቁጣ (፪x) በእሳት ቅጥሩ ቀጠረኝ ጠላት በበቀል ሳይወጣ (፪x)

ስልጣን የለውም በኔ ላይ አለቃ አይሆንም የበላይ እንዲያው አይደለም መጓደዴ በመስቀል ሞት ነው መወለዴ (፬x)

አዝ የሞት አዋጅ አይሰራም በሕይወቴ አይሆንም በሕይወቴ ገልብጦታል ነገሩን አባቴ የሞት አዋጅ አይሰራም በሕይወቴ አይሆንም በሕይወቴ ገልብጦታል ኢየሱስ አባቴ

የስንቱን ጀግና ቤት ደፍሮ መቅሰፍቱን ይዞ ሲገባ (፪x) አሳየኝ ገና ከሩቁ አጥፊውን ገዳዩን ሌባ (፪x) ሸንጐ ሰብስቦ ሲመክር ታሪኬን መና ሊያደርገው (፪x) ምልክት ሰጥቶ አስመለጠኝ እኔ የማመልከው እንዲህ ነው (፪x)

ስልጣን የለውም በኔ ላይ አለቃ አይሆንም የበላይ እንዲያው አይደለም መጓደዴ በመስቀል ሞት ነው መወለዴ (፬x)

አዝ የሞት አዋጅ አይሰራም በሕይወቴ (አይሰራም በሕይወቴ) አይሆንም በሕይወቴ (አይሆንም በሕይወቴ) ገልብጦታል ነገሩን አባቴ (ኢየሱስ አባቴ) (፪x)