Mesfin Gutu/Endihu Bewaza/Tesfayie

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ መስፍን ጉቱ አልበም እንዲሁ በዋዛ

ተስፋዬ ነህ አንተ ማረፊያዬ አንተ መታመንስ አንተ ኦ መመኪያ ነህ አንተ መመኪያዬ (፰x)


ተስፋዬ አንተው ነህ ንጉሤ አንተው ነህ አምላኬ አንተው ነህ ወዳጄ አንተው ነህ የሚሳንህ የለም ንገሥ የሚያቅትህ የለም ንገሥ የሚሳንህ የለም ክበር የሚያቅትህ የለም ክበር

በበረሃ ጋሻ ለተጠማ እርካታ ስትሆን አየሁህ የሱስ የእኔ ጌታ ጀርባህን ለደካማ ለበረታው ፊትህን ሰጥተህ አታደላም ሥምህ ብሩክ ይሁን (፭x)


ለታላቅነትህ እቀኛለሁ ለጌትነትህም እሰግዳለሁ (፫x) ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x)

የምስኪኑን ጥሪ ጩኸት ትሰማለህ በባዕድ ምድር ላይ አባት ትሆናለህ የተገፋን ማንሳት ማክበር ልማድህ ነው በሠማይ በምድር እንዳንተ ያለ ማነው (፬x)

ለታላቅነትህ እቀኛለሁ ለጌትነትህም እሰግዳለሁ ፫x) ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x)

ተስፋዬ ነህ አንተ ማረፊያዬ አንተ መታመንስ አንተ ኦ መመኪያ ነህ አንተ መመኪያዬ (፰x)