Mesfin Gutu/Endihu Bewaza/Egziabhieren Bemetemamen
< Mesfin Gutu | Endihu Bewaza
ዘማሪ መስፍን ጉቱ
ርዕስ እግዚአብሔርን በመተማመን
አልበም እንዲሁ በዋዛ
ኧረ ስንቱ በአንተ ታለፈ
የእኔ ጌታ በአንተ ታለፈ (፪x)
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ
ኃይላቸውን ያድሳሉ
እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ
መስሎት ነበር ጠላቴ ደክሜ የምቀር
እግዚአብሔር ግን በረታኝ ሆነልኝ ግርማ ሞገስ
ዛሬ ይኸው ዘምራለሁ ድካሜን ረስቻለሁ
ሥምህን አከብራለሁ ንገሥ እልሃለሁ (፪x)
አልደከምኩም አልታከትኩም ጌታ ሆኖኝ ኃይሌ
ዘለዓለም አመልከዋለሁ ኢየሱስ ጌታዬ
በደስታ በዕልልታ በአክብሮት ደግሞም በሆታ
ሥምህን አከብራልሁ ንገሥ እልሃለሁ
<\poem>