ደጅ ፡ እጠናለሁ (Dej Etenalehu) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 7.jpg


(7)

የታመንኩትን ፡ አውቃለሁ
(Yetamenkuten Awqewalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

አዝ፦ አንተ ፡ እስከምታየኝ ፡ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም ፡ አልሄድም ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ (፪x)

ካህኑ ፡ ኤሊ ፡ እንኳን ፡ ምንም ፡ ባይረዳት
እንደምናምንቴ ፡ ሰካራም ፡ ቢቆጥራት
ሃና ፡ በአንተ ፡ ፊት ፡ እንባዋን ፡ ስታፈስ
ሳሙኤልን ፡ ሰጠሃት ፡ የልመናዋ ፡ መልስ

አዝ፦ አንተ ፡ እስከምታየኝ ፡ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም ፡ አልሄድም ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ (፪x)

በምድረበዳ ፡ ውስጥ ፡ ብቻዋን ፡ እያለች
አጋርን ፡ የሚያያትን ፡ በዓይኖቿ ፡ አየች
እኔም ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አንተን ፡ ጠብቃለሁ
በረሃውም ፡ ምንጭን ፡ ሲያፈልቅ ፡ አየዋለሁ

አዝ፦ አንተ ፡ እስከምታየኝ ፡ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም ፡ አልሄድም ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ (፪x)

ማንም ፡ ባይረዳ ፡ የልቤን ፡ የውስጥ ፡ ችግር
ጀሮ ፡ ዳባ ፡ ቢሉኝ ፡ ልናገር ፡ ስሞክር
ልታስወግድ ፡ የለም ፡ፊቴም ፡ በእንባ ፡ ይራስ
የአንተ ፡ ጊዜ ፡ ደርሶ ፡ እስክታሰብ ፡ ድረስ

አዝ፦ አንተ ፡ እስከምታየኝ ፡ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም ፡ አልሄድም ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ (፪x)

ያየሁት ፡ ራዕይ ፡ በልጅነት ፡ ወራት
የማይሞላ ፡ቢመስል ፡ ቢያስቆጥር ፡ ዓመታት
የአንተ ፡ ጊዜ ፡ ሲደርስ ፡ ንጉሥ ፡ ያስኩቸኩላል
የመከራው ፡ ዘመን ፡ በክብር ፡ ይተካል

አዝ፦ አንተ ፡ እስከምታየኝ ፡ እስከምትጐበኘኝ
ወዴትም ፡ አልሄድም ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ (፪x)