From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አንነቃነቅም ፡ እንቆማለን
መሠረታችን ፡ አለት ፡ ነው
ዓለቱም ፡ ኢየሱስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)
ማዕበል ፡ ቢነሳ ፡ ወጀብም ፡ ቢመጣ
አይሎ ፡ ቢታይም ፡ የቆመ ፡ ባላንጣ
የሕይወት ፡ መሰረት ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ አለቱ
በእርሱ ፡ አንጸናለን ፡ ብንገባም ፡ ከእሳቱ
አዝ፦ አንነቃነቅም ፡ እንቆማለን
መሠረታችን ፡ አለት ፡ ነው
ዓለቱም ፡ ኢየሱስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)
የማዕበሉ ፡ አዛዥ ፡ የሁሉ ፡ ፈጣሪ
ብርቱ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ ፡ ፈጣሪ
እንናገራለን ፡ በእርሱ ፡ እንደፍራለን
በዘላለም ፡ አባት ፡ በጸጋው ፡ እንቆማለን
አዝ፦ አንነቃነቅም ፡ እንቆማለን
መሠረታችን ፡ አለት ፡ ነው
ዓለቱም ፡ ኢየሱስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)
ስማ ፡ ዲያብሎስ ፡ ሆይ ፡ የጨለማው ፡ አውራ
እኛ ፡ እንደነግጥም ፡ ብትነዛ ፡ ጉራ
መለከት ፡ ብትነፋ ፡ በዓለም ፡ ብታጮኸው
በዓለት ፡ እንቆማለን ፡ እንተን ፡ በሚፈጨው
አዝ፦ አንነቃነቅም ፡ እንቆማለን
መሠረታችን ፡ አለት ፡ ነው
ዓለቱም ፡ ኢየሱስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)
ይሄ ፡ ነው ፡ ሚስጢሩ ፡ የመስቀሉ ፡ ጉልበት
የማይነቃነቅ ፡ ደም ፡ የፈሰሰበት
ክብር ፡ ዋጋ ፡ ያለው ፡ ድንቅ ፡ የጌታችን ፡ ስም
አያሳፍረንም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ዘላለም
አዝ፦ አንነቃነቅም ፡ እንቆማለን
መሠረታችን ፡ አለት ፡ ነው
ዓለቱም ፡ ኢየሱስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)
|