Meserete Kristos Choir/Oh Girum Hayl New/Tenestual

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ተነሥቷል (፪x) የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሏል ከፈኑ ብቻ ነው አስክሬኑ የታል? በእውነትም ኢየሱስ ድል ነሥቷል (፪x)


1. ኢየሱስ ማሸነፉን ይስማ ኢየሩሳሌም

ይውጣ ምሥራቹ ከዓለም እስከዓለም

ይስማ እንጂ ጠላት መርዶውን አልቅሶ

ጌታ እንደው ተነስቷል አይሞት ተመልሶ


2. ይወገድ ድንጋዩ ጠባቂውም ይምጣ

ኢየሱስን ካቃተው ጌታ መውጫ ካጣ

የትኛው ጠባቂ ነው የከለከለው

ጌታ መቃብሩን ሲፈነቃቅለው


3. ይነገር ለዓለም ምስራች ይሰማ

ሞትን አሸንፏል ጀግናው ኢየሱስማ

ይህ ሐሰት አይደለም ዘለዓለም እውነት ነው

ይታይ የጌታችን መቃብር ባዶ ነው


4. ይሄ ነው እንግዲህ የጐልጐታው ሚስጥር

ወንጌላችን ኢየሱስ ከሙታንም በኩር

ሙትን አናመልክም መቃብር የዋጠ

ያሸነፈን እንጂ ሞትን ድል የነሳ


አዝ ተነሥቷል (፪x) የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሏል ከፈኑ ብቻ ነው አስክሬኑ የታል? በእውነትም ኢየሱስ ድል ነሥቷል