እስከዛሬ ፡ አብረን ፡ ሳለ (Eskezarie Abren Sale) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 6.jpg


(6)

ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው
(Oh Girum Hayl New)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 3:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

የደን ልማቱ የገደል ስርገቱ

      የወንዝ ርዝመቱ የቀላይ ውበቱ

      የቆንጆ ገፅታው የቦታ ከፍታው

      የባህር ጥልቀቱ የሜዳ ስፋቱ

      እኛ የምናመልከው መሠረቱ

እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ የምናመልከው

      እንደምን ኃያል ነው እኛ ምንሰግድለት

የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት

 

    የሽቶ መዓዛው የሙዚቃ ቃናው

      የለምለም እርካታ የመዝናኛ ቦታ

      የመፋቀር ወዙ የትዳር ማገዙ

      የፍጥረት ድምቀቱ የሰማይ ርቀቱ

      እኛ የምናመልከው መሠረቱ

 

    የአበቦች ፍካታ የወፎች ጫጫታ

      የቀለም መዋሃድ የሰው ልጅ መዋደድ

      የዕምንነተ እርካታ ሰላምና ደስታ

      የፅዮን ውበቱ የእውነት ጥራቱ

      እኛ የምናመልከው መሠረቱ

 

    ጎህ ሲቀድ ማለዳ ጨለማ ሲከዳ

      የፀሐዩ ሙቀት የከዋክብት ብዛት

      የደመናት ክምር ንጹህ ተስማሚ አየር

      ሁሉን በስርዓቱ መሪ ለፍጥረቱ

 

      እኛ የምናመልከው መሠረቱ