ብዙ ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩ (Bezu Bezu Feqru) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 6.jpg


(6)

ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው
(Oh Girum Hayl New)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

ብዙ ብዙ ፍቅሩ ብዙ ብዙ ምህረቱ
ብዙ ብዙ ቸርነቱ አቆመኝ በቤቱ

 ጌታ ብዬ የምጠራው አዲስ ቅኔ የምቀኘው
     እግሬም ፀንቶ የቆመው በእኔ አይደለም በእርሱ ነው
      ምህረቱ ብዙ ነው

በብርቱ ሰልፍ ያቆመኝ በውጊያ ድል የሰጠኝ
   ኃጢአት ስትከበኝ በድካሜ እያገዘኝ
      ፍቅሩን እያሳየኝ

   በጠላቴ ፊት ለፊት ራሴን ሲቀባ ዘይት
    ሲያስተናግደኝ ተግቶገበታን አዘጋጅቶ
     ቸርነቱ በዝቶ

  መድኃኒቴን ሳስከፋ ገበታውን ስደፋ
    ማረኝ ብዬ ግን ሳለቅስ በእጆቹ በመዳሰስ
      እንባዬን በማበስ

   እግዚአብሔር አባቴ ይክበር ይንገሥ በሕይወቴ
     ይህንን አይቻለሁ ጌትነቱ የፍቅር ነው
       ፍጥረት ሁሉ ያንግሰው