በደስታ ፡ ሃሌሉያ (Bedesta Haleluya) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
(Meserete Kristos Choir)

Meserete Kristos Choir 6.jpg


(6)

ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው
(Oh Girum Hayl New)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች
(Albums by Meserete Kristos Choir)

በደስታ ሃሌሉያ በእልልታ አሜን (2)

ጌታ መገለጡን እጠብቃለሁ

 

    ጌታችን ሊገለጥ ተዳርሷል ሰዓቱ

      የተሰጠን ተስፋ ሊሞላ ትንቢቱ

      ሊታመን በቃሉ ጥቂት አይዘገይም

      ፍጥረታት ቢጠፉ ቃሉ ግን አያልፍም

 

    ፀሐይቱ ስትጨልም ጨረቃዋም አብራ

      ከዋክብት ሊጠፉ ሊመጣ መከራ

      የምድር ሃያላት ሁሉ ሊናወጡ

      ጭንቀትም ሲበዘ ድንጋጤ ምጡ

 

    የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ሊሉ

      ኢየሱስን ከላይ ከሰማይ ያያሉ

      ጌታችን ሲገለጥ በክብር በግርማ

      እኛ አንሸበርም የመጣው ለኛ ነው

 

    ሊወስደን ከቦታው ካበጀልን ሥፍራ

      ባባቱ ዙፋን ሥር በፅዮን ተራራ

      ከምድር መከራ ሊሰጠንም እረፍት

      መሄዳችን አይቀር ቢመስልም ሞኝነት

 

             በእምነት ሃሌሉያ በተስፋ አሜን

 

መሲሁ ሲገለጥ እንነጠቃለን