ጥሪ አለው፡ ለአንተ (Teri Alew Lante) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ጥሪ አለው ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ፊትህን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)
በዓለም ፡ መኖርህ ፡ የታል ፡ ደስታው
ነፍስህ ፡ እረፍትን ፡ መቼ ፡ አይታው
ተው ፡ ልብ ፡ ብለህ ፡ ስማኝ ፡ ወንድም
ምን ፍሬ አገኘህ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም (፪x)
አዝ፦ ጥሪ አለው ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ፊትህን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)
ሰላም ፡ አለኝ ፡ ብትል ፡ ትዋሻለህ
ደስታ ፡ አለኝ ፡ ብትል ፡ ትቀጥፋለህ
ከጌታ ፡ እርቆ ፡ እረፍት ፡ የለም
ውስጥህ ፡ ያውጠንጥነው ፡ ተው ፡ ግድ ፡ የለም (፪x)
አዝ፦ጥሪ አለው ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ፊትህን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)
ብትጠላው ፡ እንኳን ፡ ያፈቅርሃል
ክፋትህን ፡ እንዲያይ ፡ መች ፡ ይወዳል
ፊትህን ፡ አዙረህ ፡ ብትሸሸው
እጁ ፡ እስኪያገባህ ፡ ትዕግስት ፡ አለው (፪x)
አዝ፦ ጥሪ አለው ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ፊትህን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እንድትመልስ (፪x)
|